ሰላምታ ለሚስቴ

Wednesday, 03 August 2016 14:02

 

ውዷ ባለቤቴ ሰላም እልሻለሁ

በናፍቆት ጠብቂኝ ሰክሬ መጣለሁ

እኔ ሰማይ ነካሁ ፈልጊኝ ከመሬት

አንቺ ኮሶ ሁኚ እሆናለሁ እሬት

ቤንዚን ሆነሽ ቆይኝ እኔ እሳት ሆኛለሁ

ካልታመምሽ ያመኛል ካላዘንሽ አዝናለሁ

አንቺ የፍቅር ማግ እኔ የነገር ድር

በጊዜ ና! በይኝ ከቤትም አላድር

ብትከፊ ልሳቅ ብትስቂም ልከፋ

ያንቺ አፍ ሲከፈት የኔ ጆሮ ይጥፋ።

ፍቅር - በታገል ሰይፉ

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
491 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ መስከረም አያሌው

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us