የውሻ ወተት ሱሰኛው ታዳጊ

Wednesday, 03 August 2016 14:05

 

ሞኒት ኩማር የ10 ዓመት ህንዳዊ ታዳጊ ነው። ይሄ ታዳጊ ባለፉት ስድስት ዓመታት የውሻ ወተት ሲጨልጥ ያደገ ታዳጊ ነው። ወተቱን የሚጠጣውም ቀጥታ ከውሾቹ ጡት በመጥባት ነው። እስከ ሁለት ዓመቱ ድረስ በቤት ውስጥ እንክብካቤ ሲደረግለት ያደገው ሞኒት ልክ አራት ዓመት ሲሞላው ግን ውሾችን እያሳደደ ጡታቸውን የመጥባት ለየት ያለ ባህሪይ ማሳየቱን ወላጆቹ ተናግረዋል። ወላጆቹ ከዚህ ድርጊቱ ለመታደግ ከቤት እንዳይወጣ ከዚያ አልፎም ትምህርት ቤት እንኳን እንዳይሄድ ለማድረግ ሞክረዋል። ነገር ግን ሞኒት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህን ድርጊት ከመፈፀም አልቦዘነም። አሁን አሁንማ ውሾቹም ለምደውት እርሱን እየተከተሉ እየመገቡት ነው ብለዋል።

 

አብዛኞቹ የአካባቢው ሴት ውሾች ልክ እንደ ልጃቸው ጡታቸውን ለሞኒት ለማጥባት ፈቃደኛ እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የአካባቢው ሰወችም የልጁን ድርጊት በመቃወም ለወላጆቹ መቀሳ በተደጋጋሚ ያቀርባሉ ተብሏል። ሞኒት በአንድ ወቅት በአንዲት ውሻ ከመነከሱ ውጪ እስካአሁን ድረስ ከዚህ ጋር በተያያዘ የደረሰበት ጉዳት የለም ተብሏል። ከጉዳቱ ለመዳንም እና ለእብድ ውሻ በሽታ እንዳይጋለጥ ህክምና ከማግኘት የዘለለ የተደረገለት ነገር አልነበረም። የህክምና ባለሙያዎች እንዳሉትም የውሻ ወተት በተፈጥሮው ለሰው ልጅ መርዛማነት የለውም። ነገር ግን ለእብድ ውሻ በሽታ የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው። ይሄ እውነት ቢነገረውም ሞኒትን ግን የሚያስቆመው ነገር አልተገኘም ይላል የደይሊሜል ዘገባ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
474 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us