ህብረ ቃል አፈር ነው

Wednesday, 10 August 2016 13:44

ብርሃኑማ እኩል ነው፤ ለአዳምነት ፍርዱ

ቀን አዋርዶት አየው፤ መሸበት ላንዳንዱ፤

የዕለት ጉርሱ ግርዶሽ፤ ዘመኑ የተስፋ ዕዳ

ሆዱን ሳይችል ያድራል፤ ደሃ በልቶ ፍዳ፤

ህይወት ተሸከርካሪ፤ በፊት እና ጀርባ

አንዱ ጎዳና  ነው፤ ሌላው ቤት ሲገባ፤

እንደ ሰው ተፈጥሮ፤ ሰው መሆን ያልቻለ

ስንት አለ እራቁታም፤ ልብሱን የመሰለ፤

ምቾት እያጠናው፤ ኑሮ ተመቻችቶ

ቢያሻው ከምድር ላይ፤ ሲለው ካየር ወጥቶ

ከደሥታው ባህር፣ የሚኖር እንደ ዓሣ

ስንት አለ ባለ ሥም፤ ወገኑን የረሳ፡

የት ትሆን ወዳጄ፤ ንገረኝ ቅጥርህን

አቅም አለህ ለማወጅ፤ ውሎ እና አዳርህን?

ነብስህ ቅኔ ቢሆን፤ ወርቅ እና ሰም ሆኖ

ህብረ ቃል አፈር ነው የሚኖር ዘላለም ካንተ በላይ ገኖ።

                  የራስ ዕዳ - በገዛኸኝ ታደሰ

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
529 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us