አሣን ያስናቁን ዋናተኞች

Wednesday, 10 August 2016 13:45

የአለማችን በትንሽ እድሜ የዋና ሻምፒዮናዋ ሴት አልዛይን ታሪቅ ትባላለች። ይህች ታዳጊ ገና በአስር አመቷ ነበር ለዚህ ክብር የበቃችው። ታዳጊዋ በ2015 ዓ.ም ለዚህ ክብር የበቃች ሲሆን፤ የሐምሳ ሜትር ርቀት ዋናን በቢራቢሮ ቀዘፋ ማጠናቀቅ የቻለችው በ41 ሰከንድ ከ13 ማይክሮ ሰኮንዶች ውስጥ ነበር። ይህ ክብር ወሰን እስከ አሁን ድረስ የደረሰበት የለም።

በዚህ በ2015 ከዚህች ታዳጊ በተቃራኒ የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙት ጃፓናዊም አለምን ያስደነቀ ተግባር ፈፅመዋል። ሚያኮ ናጋዝኦካ ከዚች ታዳጊ በዘጠና አመት ይበልጣሉ። ሆኖም ግን እድሜ ሳይገድባቸው ስማቸውን በአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ማስፈር ችለዋል። እኒህ የእድሜ ባለፀጋ በመቶ አመታቸው 1ሺህ 500 ሜትር ርቀትን በዋና በማጠናቀቅ የሚያክላቸው በመጥፋቱ ስማቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

ዲያና ኒያድ ትባላለች። ይህች ሴት እድሜዋ 64 አመት ሲሆን፤ በዋናው ዘርፉ እስከዛሬ ተፎካካሪ ያላገኘች ሴት ናት። ዲያና ከኩባ እስከ ፍሎሪዳ ያለውን ርቀት በዋና በማካለል ነው ለዚህ ክብር የበቃችው። ዲያና ይህን 103 ማይልስ ርቀት በዋና ያለማቋረጥ በማጠናቀቋ እስከ አሁን ድረስ ክብረ ወሰኑን በእጇ አድርጋለች። ለዚህ ክብር ለመብቃትም ከስድስት ጊዜ ያልተናነሰ ሙከራ ማድረጓ ተገልጿል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
295 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us