ምርጥ አባባሎች

Wednesday, 17 August 2016 12:11

 

 ·         የብርሃን ፍነትን ሳይቀር ማስላት እችላለሁ። ነገር ግን ከፈገግታ ጀርባ ያለውን የሰው ልጅ ጥላቻ ማስላት አልችልም። (አልበርት አንስታይን)

·         እያንዳንዱን ቀን የመጨረሻ ቀንህ እንደሆነ እያሰብክ ከኖርክ በእርግጠኝነት አንድ ቀን ሀብታም ትሆናለህ። (ስቲቭ ጆብስ)

·         መልካምነት የህይወትን ማዕበል የመቋቋሚያ ብቸኛው አገልግሎት እና መቼም ቢሆን ታጥቦ የማይሄድ ነው። (አብርሃም ሊንከን)

·         አለማችን አደገኛ የሆነችው መጥፎ በሚሰሩ ሰዎች ምክንያት ሳይሆን ምንም ሳይሰሩ ዝም ብለው በሚመለከቱ ሰዎች ምክንያት ነው። (አልበርት አንስታይን)

·         ፍቅር ጠላትን ወደ ጓደኛ የመቀየሪያ ብቸናው ሃይል ነው። (ማርቲን ሉተር ኪንግ)

·         ትክክለኛ ውሳኔ በመወሰን አላምንም። ይልቁንም ውሳኔዎች ትክክል እንዲሆኑ በማድረግ አምናለሁ። (ራታን ታታ)

·         በእግር ጣታችን የምንራመድ ከሆነ ዱካ ልንተው አንችልም (ሎትራን ኦቦቴ)

·         ሽንፈት የአንጎል ጉዳይ ነው። ማንም ሰው ሽንፈት እውነት መሆኑን አስካልተቀበለ ድረስ ሊሸነፍ አይችልም (በሩስ ሊ)

·         ብልፅግና የማይቀር የጠንካራ ሰራተኝነት ውጤት ቢሆን ኖሮ የአፍሪካ ሴቶች በሙሉ ሚሊኒየር በሆኑ ነበር። (ጆርድ ሞንቢኦት)

·         ሌሎችን ማገልገል በምድር ላይ ለምንኖርበት ክፍል የምንከፍለው ኪራይ ነው፤ (ሞሀመድ አሊ)

·         ከሰዎች ይልቅ ለእንስሳት ርህራሄን ማሳየት ቀላል ነው። እንስሳት በፍጹም አይጨክኑም (ሀይለስላሴ)

·         እውነት እንድትጨቆን ለሚፈልጉ ሰዎች መጽሐፍት እና ሌሎች የተጻፉ ነገሮች ያሸብሯቸዋል (ዎሌ ሾይንካ)

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
1161 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ መስከረም አያሌው

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us