እንዲህ ነበር

Wednesday, 17 August 2016 12:19

 

ቀደም ባሉት ጊዜያት የተከናወኑ እና ታሪክም የማይረሳቸው በርካታ በወቅቱ ትክክል የነበሩ ክስተቶች አሉ። እነዚህ ክስተቶች በወቅቱ ባለው የሰው ልጅ አስተሳሰብ መጠን ትክክል የነበሩ ነገር ግን ከጊዜ መለወጥ ጋር እየተለወጡ የሚመጡ ናቸው። እነዚህ እውነታዎች እና ክስተቶች ጊዜው ካለፈ በኋላ ሲታዩ ከአስገራሚነታቸው ባለፈም በዚያን ጊዜ የነበረውን የሰው ልጅ አስተሳሰብ ለመገመት ያግዛሉ። እስኪ ከእነዚህ አስገራሚ ነገሮች የተወሰኑትን እንጥቀስ፡-

·         መካከለኛው ዘመን ተብሎ በሚጠራው ዘመን ሰዎች በጥንቆላ ስራ ላይ ተሰማርተው ከተገኙ በሞት እንዲቀጡ ይዳረግ ነበር። በዚህም ሳቢያ በአንድ ወቅት 600ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን እንዲያጡ ተደርጓል።

·         ሳንታ እና የተባሉት የሜክሲኮ ጀነራል የተቆረጠ እግራቸውን ለመቅበር ብሔራዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት አዘጋጅተው ነበር።

·         ጥንት ሮማዊያን የሰው ሽንት ጥርስን ነጭ ያደርጋል ብለው ስለሚያስቡ አፋቸውን በሰው ሽንት ያፀዱ ነበር።

·         በመካከለኛው ዘመን ፍርድ ቤት የሚቀርቡት ጥፋተኛ ሰዎች ብቻ አልነበሩም። ይልቁንም እንስሳትም ፍርድ ቤት ቀርበው የፍርድ ውሳኔ የሚተላለፍባቸው ሲሆን፤ ቅጣቱም እደየጥፋታቸው እስከሞት የደረሰ ነበር።

·         የበረዶ ዘመን በሚባው ዘመን ሰዎች የሞቱ ሰዎችን የራስ ቅል እንደ ሲኒ ይጠቀሙበት ነበር።

·         በአውሮፓ በአንድ ወቅት ድመቶች ከመጥፎ አምልኮ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ተጠራርገው እንዲወገዱ ተደርጎ ነበር። ይሄንን የድመቶች መጥፋት ተከትሎ የተመረዙ አይጦች በመብዛታቸው እጅግ አደገኛ በሽታ በመላው አውሮፓ ተቀስቅሶ ነበር። በዚህ ወረርሽኝም 10 ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

·         የአዜቲክስ ህዝብ ለሚያመልኩት ጣኦታቸው የሰውን ልጅ የመሰዋት ልምድ ነበራቸው። በዚህም መሠረት በአንድ ወቅት 20 ሺህ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

·         በመካለኛው ዘመን በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች የሚመረመሩት እጃቸውን በፈላ ውሃ ውስጥ እንዲከቱ በማድረግ ነበር። የፈላ ውሃ ውስጥ እጁን ከቶ እጁ ያልተላጠ ሰው ጥፋተኛ ባለመሆኑ ፈጣሪ ጠብቆት ነው ስለሚባል በነፃ ይለቀቃል።

·         ካብላ ክሃን የተባለ ሰው 5ሺህ ውሾች የነበሩት ሲሆን፤ በታሪክም የሱን ያህል ውሻ ያለው ሰው አልነበረም። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
454 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ መስከረም አያሌው

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us