እሾህን በሾህ

Wednesday, 24 August 2016 13:55

ፓስኳል ባሮኮ ኗሪነቱ አሪዞና ግዛት ሲሆን፤ የሚታወቀውም ከመጠን ባለፈ ውፍረቱ ነው። የ31 ዓመቱ ፓስኳል ይሄንን ቅጥ ያጣ ውፍረት ለመቀነስ የወሰደው እርምጃ ደግሞ አለምን እያነጋገረ ይገኛል።

ፓስኳል ግዙፍ እና 605 ፓውንድ ክብደት ያለው ሰው ነው። ይሄን ክብደቱን ተከትሎ ለከፍተኛ የደም ግፊት እና ለኮሌስትሮል ክምችት በመጋለጡ ህይወቱ ላይ አደጋ መጋረጡን በመጥቀስ ዶክተሮች ክብደቱን እንዲቀንስ አስጠንቅቀውታል። ፓስኪልም ስጋት ስለገባው ክብደቱን ለመቀነስ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ወሰነ። ነገር ግን የእርሱ ነገር አሳሳቢ ሆነበት። ወደስፖርት ቤት እንዳይሄድ ክብደቱ የስፖርት ማሽኑ ከሚችለው በላይ በመሆኑ የተለየ መላ ማፈላለግ ጀመረ። በስተመጨረሻ የደረሰበት ውሳኔም ረሃብ በሚሰማው ሰዓት በየእለቱ ምግቡን ለማምጣት በአቅራቢያው ወደሚገኝ ዎልማርት የእግር ጉዞ ማድርግ ነበር። በዚህም መሠረት በቀን ሶስት ጊዜ ዎልማርት ደርሶ ምግቡን ይዞ የሚመጣ ሲሆን፤ በዚህም በአጠቃላይ በቀን 6 ማይልስ ርቀት በእግሩ ይጓዛል። በዚህ ድርጊቱም ሁለት አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ከ200 ፓውንድ በላይ ክብደት መቀነስ ችሏል። ይሄንን ያህል ክብደት ሲቀንስ ሰውነቱ ለስፖርት ማሽኑ ተመጣጣኝ በመሆኑ ከእግር ጉዞው ጎን ለጎን ወደ ስፖርት ቤት የገባ ሲሆን፤ ለውፍረት የዳረጉትን የምግብ አይነቶችም መቀነሱን ተናግሯል።

በሁለት ዓመት ውስጥ 300 ፓውንድ ክብደት መቀነስ የቻለው ፓስኪል በአሁኑ ወቅት ትክክለኛ ክብደቱ 330 ፓውንድ ነው። ክብደቱ ሲቀንስ የሟሸሸውን ሰውነቱን ተከትሎ ቆዳው የተንጠለጠለ ሲሆን፤ ይሄ ቆዳው ብቻውን 30 ፓውንድ ክብደት አለው። በመሆኑም ይሄንን ቆዳውን በቀዶ ህክምና አስወግዶታል ያለው ኤቢሲ ኒውስ ነው። 

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
411 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us