ጥሬ ጨው

Wednesday, 31 August 2016 12:20

 

እውትም “ጥሬ ጨው

ጥሬ ጨው - ጥሬ ጨው

መፈጨት - መሰለቅ መደለዝ መወቀጥ

መታሸት - መቀየጥ ገና እሚቀራቸው. . .”

      ወይ ድንጋይ ያይደሉ

      ወይ ጨው ያልተባሉ

      ፊደል የቆጠሩ

      ግን አንድ ያልተማሩ

      ስማቸው ከፊት ፊት

      ሥራቸው ከኋሊት

      የሚጠቅም ፍሬ ትሩፋተ ቢሶች

      የደረቁ ዛፎች

      እንግሊዝ የጠጡ

      ግን እውቀትን ያጡ

እንዲያው እምቡር እምቡር እያሉ አለሁ ባዮች

ከእውቀት የጎደሉ የልብስ አራጃዎች

በፀሐይ መውጫ ላይ ዳፍንት እየሆኑ

በየመድረኩ ላይ ጩኸት የተካኑ

ካረጀ ዘመን ላይ ድንገት የቀረሩ

ግዑዝ ቀለም እንጂ ህይወት ያልተማሩ

ግፍ! ነውር! ጭቆናን በአንቀልባ እያዘሉ

ለየባለግዜው ንሴብሆ እሚሉ

ደቂቀ ይሁዳ እውት ላይ ጦር አዝማች

መክሊት እየሸጡ የደም መሬት ሸማች

የጀነትን መንገድ እዝነት የማያውቁ

የሄዱ መስሏቸው ግን እሚንፏቀቁ

በበሉበት ጯሂ መንፈስ መናና

ተምረው ያላወቁ ባዶ ገረወይና

እውነትም ጥሬ ጨው

ጥሬ ጨዋዋዎች. . . 

            ጽሞና እና ጩኸት - በሰለሞን ሞገስ 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
512 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 931 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us