የማያልቅባቸው አለቃ

Wednesday, 31 August 2016 12:18

ቀልድ አዋቂው አለቃ ገብረ ሃና መልከ መልካም እና ድምፀ መልካም ቢሆኑም ቁመታቸው ግን አጭር ነበር። በቁመታቸው ማጠር የተነሳ የሚጠቀሙባት ጭራ ትንሽ ነበረች። በዚያን ጊዜ ደግሞ ትልቅ ጭራ ማንዘርፈፍ የጨዋነት መለኪያ ሆኖ ይቆጠር ነበር። ይህን የሚያውቅ አንድ ግዙፍ መኮንንም “እንዴት እርስዎን የሚያክል ሰው ይቺን ቆራጣ ጭራ ይይዛል? ለእርስዎ የምትገባ አይደለችም” አላቸው አለቃም “ለኔ ፊት እንደሁ ትበቃኛለች። ደንቢያ አልከለከልባት” ሲሉ መለሱለት።

አለቃ በቀድሞው ራጉኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ቤት ተሰርቶላቸው አቋቋምና መርገድ እያስተማሩ ከቆዩ በኋላ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ወሰኑ። ወደ ሀገራቸው ከመመለሳቸው በፊትም ልብስ እንዲሰፉላቸው ከሸማኔዎች ጋር ተዋዋሉ። ከጥቂት ቀናት በኋላም አለቃ በበቅሎ ታጅበው ወደቤተመንግስት ሲወርዱ ሸማኔዎቹ አዩዋቸው። ሸማኔዎቹ “ጃንሆይ የሚያከብሯቸው ቄስ መጡ” ብለው ፈጥነው ከተቀመጡበት ሲነሱ አንዱ ሸማኔ ፈሱ አመለጠው። ይሄን ነገር በጆሯቸው የሰሙት አለቃ ሆዬም “ልብሱን እስካሁን ሳትሰፉልኝ መቆየታችሁ ሲገርመኝ አሁንማ እስከመቋጠሩም ተዋችሁት” ብለው በነገር ወጋ አድርገዋቸው አለፉ።

አለቃ ከቀልድ አዋቂነታቸው በተቃራኒ በትዳራቸው ላይ የመስረቅ አመል ነበራቸው። ይሰርቁ የነበረው ደግሞ ከቤት ሰራተኛቸው ጭምር ነበር። ታዲያ አለቃ አንድ ቀን ሠራተኛቸው ዘንድ ጉድ ጉድ ብለው ሲመለሱ ባለቤታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያ አድፍጠው ይጠብቁ ኖሮ በፍልጥ ወገባቸውን ለመጧቸው። አለቃ ግን ያልተመቱ መስለው እንደምንም መኝታቸው ላይ ወጡና “ምንድን ነው የወገርሽው ማዘንጊያ?” ሲሉ ጠየቋጨው። ማዘንጊያም “ኧረእንጃ አንቱ፣ ጥጃ መሳይ ነው መሰለኝ” ሲሉ መለሱላቸው። ከዱላው ይልቅ ስድቡ የከነከናቸው አለቃም፤ “ታዲያ ድርቅ ጥጃ ውስጥ መቼ አነሰውና ነው በፍልጥ የመታሽው” በማለት ጀርባቸውን ሰጥተዋቸው አደሩ።

አለቃ ገ/ሀና እና አስቂኝ ቀልዳቸው

                                                በአረፈአይኔ ሀጎስ  

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
1609 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 119 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us