ሙላህ እና ህጻናት

Wednesday, 31 August 2016 12:23

 

ስለቀልድ አዋቂው ሙላህ ኑስረዲን ከብሉ ፕላኔት ጆርናል ያገኘነውን እናካፍላችሁ። ሙላህ ኑስረዲን አህያ ላይ ተቀምጦ ሲሄድ በብይ ጨዋታ ላይ የነበሩ ህፃናት ያዩታል። ህፃናቱ ሲያዩት ግን ኑስረዲን አህያውን የተቀመጠው ወደ ጭራው ዞሮ ነው። ከህፃናቱ አንዷም “ሰላም ሙላህ፤ አህያው ላይ የተቀመጥከው ወደተሳሳተ አቅጣጫ ዞረህ  ነው እኮ” አለችው። ኑስረዲንም ከህፃኗ ቀበል አድርጎ፤ “እኔ አይደለሁም የተሳሳትኩት፤ እኔ የተቀመጥኩት በትክክለኛው አቅጣጫዬ ነው። ይልቅ ወደ ኋላ እየሄደ ያለው አህያው ነው” ብሎ ከመለሰላት በኋላ በመጣበትሁኔታ መንገዱን ቀጠለ። በቀጣዩ ቀንም ኑስረዲን በተመሳሳይ ሁኔታ አህያው ላይ ተቀምጦ ሲመጣ ህጻናቱ አዩት። በዚህኛው ቀን ደግመው ስላዩት ወደ ኋላ ዞሮ አህያው ላይ እንደተቀመጠ አረጋገጡ። ጠጋ ብለውም “ይሄ ነገር እንዴት ነው አቶ ሙላህ? አህያው ወደ ፊት እንዲሄድ ማድረግ አልቻልክም እንዴ? ሲሉ በጥያቄ አጣደፉት። ኑስረዲንም በህፃናቱ ሁኔታ በስጭት ብሎ “በድጋሚ ተሳስታችኋል። ዛሬ እኔም ፊት ለፊት ነው የተቀመጥኩት፤ አህያዬም ወደፊት ነው እየሄደ ያለው። ይልቅ እናንተ ናችሁ ወደ ኋላ እየተመለከታችሁ ያላችሁት” ብሎ መለሰላቸው።

አንድ ጊዜ ደግሞ ሁለት ህጻናት ኑስረዲንን ሊያታልሉት አሰቡና የሚከተለውን ነገር አደረጉ። ልጆቹ አንዲት ወፍ በእጃቸው ይዘው ከጀርባቸው ከደበቁ በኋላ ኑስረዲንን ወፏ በህይወት መኖሯን እና አለመኖሯን እንዲነግራቸው አደረጉ። ወፏ በህይወት አለች ካላቸው በእጃቸው ጨፍልቀው በመግደል መሳሳቱን ለማሳየት ሲሆን፤ ሞታለች ካለ ደግሞ ወፏን እንድትበር በማድረግ ሊያታልሉት ፈለጉ። በመሆኑም ወፏ መሞት እና በህይወት መኖሯን ኑስረዲንን ጠየቁት። ብልሁ ኑስረዲንም ለተወሰኑ ደቂቃዎች አሰብ አደረገና መልስ ሰጠ። “ልጆቼ የዚህች ወፍ ህይወት እኮ ያለው ከእናንተ እጅ ላይ ነው” ሲል መለሰላቸው።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
523 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 166 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us