ምርጥ የአፍሪካዊያን አባባሎች

Wednesday, 31 August 2016 12:24

 

·         በችግር ጊዜ ብልህ ሰው ድልድይ ሲገነባ፤ ሞኝ ደግሞ ግድብ ይገድባል (ናይጄሪያዊያን)

·         ሀብት ሲጠቀሙበት እያለቀ ይሄዳል፤ ትምህርት ግን እየተጠቀሙበት በሄዱ ቁጥር እየጨመረ ይሄዳል። (ስዋህሊ አባባል)

·         እውነቱን ላለማየት አይናችንን የምንጨፍን ከሆነ ልንማር የምንችለው ከአደጋ ይሆናል። (ኬኒያዊያን)

·         ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ወቅት ብዙ ትምህርት ይገኛል። (አፍሪካዊያን)

·         ሞኝ ጨዋታውን ሲለምደው ተጫዋቹ ይበተናል። (አሻንቲዎች)  

·         ምክር ልክ እንደ እንግዳ ነው። የሚቀበለው ካገኘ ያድራል፣ ካልተቀበሉት ግን የዚያኑ ቀን ተመልሶ ይሄዳል። (ኮንጎዎች)

·         አዋቂዎች በበዙበት ቦታ የአዳማጭ እጥረት አለ። (የስዋህሊ አባባል)

·         በአንበጣዎች መካከል የሚደረግ ፀብ ለከብቶች መዝናኛ ነው ( ቦትስዋናዊያን)

·         ትልቅ ወንበር ብቻውን ንጉስ ሊያደርግ አይችልም። (ሱዳናዊያን)

·         በረሮ ዶሮዎችን የመምራት ሃሳብ ካለው ቀበሮን ጠባቂው አድርጎ መቅጠር ይኖርበታል። (ሴራሊዮናዊያን)

·         ቤተሰብ ልክ እንደ ደን ነው። ከሩቅ ሲያዩት ጥቅጥቅ ያለ ሲሆን፣ ሲገቡበት ግን እያንዳንዱ የየራሱ ቦታ አለው። (ኮንጎዎች)

·         የገንዘብ ስልት ከጦር ስልት ይበልጣል። (የአሻንቲ አባባል)

·         ገንዘብ ማውራት ባይችልም ውሸትን እውነት የማድረግ አቅም አለው። (ደቡብ አፍሪካዊያን)

·         ከገንዘብ ውስጥ ስንወጣ አዋቂ እየሆንን እንሄዳለን። (ጋናዊያን)

·         እስከሚያወራ ድረስ እያንዳዱ ሰው ውብ እና ቆንጆ ነው። (ዙምባቢዎች)

ይምረጡ
(25 ሰዎች መርጠዋል)
1352 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 164 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us