ቀመር

Wednesday, 07 September 2016 13:55

 

ጎረቤት ደስታ አለ

      ቅንጦት ያደለበው

            ወፍራም ሳቅ ይነጉዳል

ከአለማችው ጣሪያ

      ከምልዐት ሰማይ

            ረድኤት ወርዷል

ላትጠልቅ የማለች

      ቃል ያላት ይመስል

            ያለ ስስት ፈግጋ

ብሩህ ናት ፀሐይዋ

      ዕልም አድማስ ጋርዷት

            አይኗ መች ተወጋ

ደመናውን ገፎ

      በብርሃን ሞገድ

            በፀጋ የመጠቀ

ተራግፎ ጭጋጉ

      ከወትሮው ማልዶ ነው

            ጎህ የፈነጠቀ

በጊዜ ጨላልሞ

      ቀናችን ጉም አዝሎ

            በኛ ቤት ሳቅ መሽቷል

ንብርብር በድን ልብ

      ትንሳኤውን ናፍቆ

            ሲዋልል ሰንብቷል

ከምኞት ካብ ናዳ

      በማጣት ቁልቁለት

            ኋሊት ተንከባለን

በውል እልባ ትብታብ

      በሀዘን ቁራኝነት

            በብሶት ታጅለን

ስንት ዘመን ስንድህ

      መቆም እንዳቃተን

            እንደቆሰልን አለን

በእድል የሚፈወስ

      በእድል የሚቆስል

ሰው ቀለም አልባ ነው

      ባለብዙ ምስል።

                  ውለዳት - በኤልያስ ቦጋለ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
348 ጊዜ ተነበዋል

ተጨማሪ ጽህፎች ከ መስከረም አያሌው

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us