አንዳንድ እውነታዎች ስለፋሽን

Wednesday, 07 September 2016 13:56

 

·         በ1800 እና በ1900 አጭር ፀጉር ያለመታመን መገለጫ ነበር። በዚህ ዘመን አጭር ፀጉር ያላት ሴት ታማኝ አይደለችም ተብላ ትጠረጠር ነበር።

·         በ19ኛው ክፍለ ዘመን የልብስ ዲዛይነሮች የሰሯቸውን የልብስ ዲዛይኖች ለተመልካች ያሳዩ የነበረው በአሻንጉሊት በመጠቀም ነበር።

·         እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ድረስ ባለው ጊዜ ሴቶች አጭር ቀሚስ በአደባባይ እንዲለብሱ አይፈቀድላቸውም ነበር።

·         የልብስ መስፊያ መርፌዎች ከ30ሺህ ዓመት በፊት እንደተሰሩ የሚገመት ሲሆን፤ በዚያን ጊዜ ይሰሩ የነበረውም ከእንስሳት አጥንት ነበር።

·         በዓለማችን ላይ በየዓመቱ 2 ቢሊዮን ካናቴራዎች ይሸጣሉ።

·         በጥንት ሮማዊያን ዘንድ ሀምራዊ ቀለም ያላቸው አልባሳት የሚዘጋጁት ለንጉሳዊያን እና ለአጥቢያ ዳኞች ብቻ ነበር።

·         በአንድ ወቅት ሀዘን ከደረሰበት ሰው በስተቀር ጥቁር ልብስ መልበስ ነውር ነበር። በዚያን ወቅት አንዲት የቪክቴሪያ ሴት ባሏ ከሞተባት ለሁለት ዓመታት ጥቁር ልብስ የመልበስ ግዴታ ነበረባት።

·         እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በነበረ ጊዜ ትንሽ እግር በቻይናዊያን ዘንድ የውበት መገለጫ ነበር። ስለዚህ ሴቶች ገና ከጨቅላ እድሜያቸው ጀምሮ እግራቸው እንዳይረዝም የማጠፍ ልማድ ነበር። በዚህም ሳቢያ በርካታ ሴቶች እግራቸው እየተጣመመ ለመራመድ የሚቸገሩ ሆነው ቀርተዋል።

·         በወንዶች ዘንድ ከመቀመጫ ወረድ ያለ ሱሪን የመልበስ ባህል የጀመረው በሎስ አንጀለስ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በዚያች ግዛት የነበሩ እስረኞች ቀበቶ መታጠቅ ስለማይፈቀድላቸው ሱሪያቸው በመቀመጫቸው ወረድ ያለ ነበር።

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
520 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 914 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us