የእድሜ ባለፀጋው ሞትን እየለመኑ ነው

Wednesday, 07 September 2016 13:58

አቶ ጎቶ ምባህ የውልደት ዘመናቸው 1870 ነው። እድሜያቸው ሲሰላ ደግሞ የ145 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ ናቸው። እኚህ ህንዳዊ የእድሜ ባለፀጋ ከሰሞኑ የልደት ሰርተፍኬታቸውን ይዘው ብቅ ብለዋል ሲል ያስነበበው ዘ አንዲፔንደንት ነው።

የአቶ ጎቶን ነገር የበለጠ አስገራሚ ያደረገው ነገር ደግሞ በዚህ እድሜያቸው እንኳን ሲጋራ ማጨስ አለማቆማቸው ነው። አቶ ጎቶ ለዚህ ረጅም እድሜ ምንም የተለየ ምስጢር እንደሌለው ነው የገለፁት። የአመጋገብ ስርዓታቸው ከሌላው ሰው የተለየ አለመሆኑን ይልቁንም ዋናው ነገር ዘና ያለ እና ቀላል ህይወት መምራታቸው መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ጎቶ አሁንም ድረስ በሙሉ ጤንነት ላይ መሆናቸውን የ41 ዓቱ የልጅ ልጃቸው ተናግሯል። የልጅ ልጃቸው እንደገለፀው አያቱ የአይናቸው እይታ እና የጆሯቸው የመስማት አቅም ቢቀንስም ሌላ የጤና ችግር ግን የለባቸውም። ቀናቸውን የሚያሳልፉትም የተሰጣቸውን ምግብ ጥርግ አድርገው በመመገብ እና ሲጋራቸውን በማጤስ ነው። ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ግን ራሳቸውን ችለው መመገብ እና መፀዳጃ ቤት መጠቀም እያቃታቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ሌላው አስገራሚው የእኚህ ሰው ታሪክ ሰውየው ለመሞት ያላቸው ፅኑ ፍላጎት ነው። አቶ ጎቶ የዛሬ 24 (በ1992) ነበር ለመሞት ዝግጁ የሆኑት። እንደሚሞቱ እርግጠኛ በመሆንም በስማቸው የመቃብር ድንጋይ አሰርተው ነበር። ነገር ግን እነሆ ከ24 ዓመታት በኋላም በህይወት አሉ። አሁንም ቢሆን ግን አቶ ጎቶ ዋናው ፍላጎታቸው መሞት እንደሆነ በተደጋጋሚ እየተናገሩ ይገኛል። ሞት በራሱ ጊዜ የሚመጣ መሆኑን ቢገነዘቡትም የእርሳቸው ፍላጎት መሞት ብቻ መሆኑን እየተናገሩ ይገኛል።

አቶ ጎቶ በዚህ የህይወት ዘመናቸው አራት ጊዜ ትዳር መስርተዋል። ከዚህ ትዳራቸው ሶስት ልጆችን የወለዱ ሲሆን፤ እርሳቸው በህይወት እያሉ ሁሉም ቤተሰቦቻቸው በሞት ተለይተዋቸዋል። አቶ ጎቶ ይህን ያህል እድሜ በህይወት መኖር በመቻላቸው በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስማቸውን ለማስፈር መታሰቡ የተገለፀ ሲሆን፤ ይህን እውነታ በምን መልኩ ማረጋገጥ እንደሚቻል ግን ግራ መጋባት ተፈጥሯል ብለዋል የዘርፉ ባለሙያዎች። እውነታውን ማረጋገጥ ከተቻለ ግን ከዚህ ቀደም በፈረንሳዊቷ ጆን ካልሜት በ122 ዓመት በህይወት በመኖር ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን ይቆናጠጣሉ ተብሏል።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
734 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 994 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us