ምርጥ አባባሎች

Wednesday, 14 September 2016 15:17

-    ስኬታችንን ማክበር ጥሩ ነው፣ ግን በጣም አስፈላጊው ነገር ከውድቀታችን ያገኘነውን ትምህርት መቀበሉ ላይ ነው። (ቢል ጌትስ)

-    የምታወጣቸው ቃላት ከዝምታ የተሻሉ መሆናቸውን ስታውቅ ብቻ ተናገር። (ያልታወቀ ፀሐፊ)

-    ራስህን በዚህ ዓለም ላይ ካለ ማንም ሰው ጋር አታወዳድር። ይሄን ካደረክ ግን ራስህን እየሰደብክ ነው። (ቢል ጌትስ)

-    አንዳንድ ሰዎች እንደ ቡራኬ ሆነው ወደ ህይወታችን ሊገቡ ይችላሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ አንደ አስተማሪ ሆነው ይመጣሉ። (ማዘር ትሬዛ)

-    በሰከንድም አሸነፍክ በማይል ችግር የለውም። ማሸነፍ ማሸነፍ ነው። (ቪን ዲሴል)

-    አንዳንድ ጊዜ ዝምታ በውስጣችን የሚካሄደውን ነገር የሚገልፅ ብቸኛ መንገድ ነው።

-    ያጣኸውን ነገር ወደኋላ በማየት ጊዜህን አታጥፋ። ወደፊት ቀጥል። ህይወት የኋሊዮሽ ጉዞ አይደለችም። (ያልታወቀ ፀሐፊ) 

ይምረጡ
(9 ሰዎች መርጠዋል)
1470 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us