በ90 ዓመት ወደ ስራ

Wednesday, 07 December 2016 14:09

እንግሊዛዊው የእድሜ ባለፀጋ በወጣትነት ዘመናቸው የሀገራቸውን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ ደፋ ቀና ሲሉ ነበር። በዚህ ተግባራቸውም ሀገራቸውና ህዝቧ ጀግና ስትል ማዕረግ ሰጥታቸዋለች። ህይወታቸውን በሙሉ በድሎት የሮሩ ሲሆን ወደማለቂያው ግን ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው። የ89 ዓመቱ ጀግና አቶ ጆይ ባርሊይ ይባላሉ። እኚህ ሰው ከሁለት ዓመታት በፊት ባለቤታቸውን በሞት በመነጠቃቸው ህይወት ባዶ ሆነችባቸው። ምን በመሰለ ቤታቸው ውስጥ ቢኖሩም ህይወት ያለበት አልመስል ስላላቸው በብቸኝነት ከምሞት ብለው መላ ማፈላለግ ጀመሩ። ለዚህ ደግሞ የነበራቸው ብቸኛ አማራጭ ስራ ተቀጥረው ስራቸውን መስራት እግረ-መንገዳቸውንም ከሰዎች ጋር መቀላቀል ነበር። ይሄን ፍላጐታቸውን በአንድ የሀገሪቱ ጋዜጣ ላይ ከገለፁ በኋላም ካንቲና ኪችን እና ባር የተባለ ምግብ ቤት አዛውንቱን ስራ አስጀምሯቸዋል። እርሳቸውም እንዲህ በቀላሉ ትኩረት ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን በመግለፅ ስራቸውን በርትተው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ሲል ያስነበበው ኤቢሲ ኒውስ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
410 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 165 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us