በ1ነጥብ 2 ሚሊዮን ታዳሚ የሚከበረው ልደት

Wednesday, 21 December 2016 14:03

 

ልደትን ማክበር በተለይ በአደጉት ሀገራት ዘንድ የተለመደ ድርጊት ነው። ልደትን በተመለከተ ከወደሜክሲኮ የተሰማው ዜና ግን አጃኢብ እያሰኘ ነው።

አቶ ሪሴንሲዮ ኢባራ የልጃቸውን ልደት ለማክበር በዝግጅት ላይ ናቸው። ይሄንን የሴት ልጃቸውን ልደት ለየት ባለ መልኩ ለማክበር በማሰብ ይሁን ምክንያቱ ሌላ ይሁን ባይታወቅም በዚህ በዝግጅታቸው ወቅት የሰሩት ስህተት ነው እንግዲህ አነጋጋሪ ያደረገው። አቶ ኢባራ የ15 ዓመት ሴት ልጃቸውን ልደት አስመልክቶ በፌስቡክ ጥሪ አቀረቡ። “ጤና ይስልኝ እንዴት ናችሁ? በመጪው ታህሳስ 26 ቀን በሚከበረው የሩቢ ኢባራ ጋርሲያ 15ኛ የልደት በአል ላይ እንድትገኙ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል” የሚል መልዕክት በፌስቡክ ገጹ ላይ ይፅፋል። እንደ አለመታደል ሆኖ አቶ ኢባራ መልዕክቱን ለህዝብ ክፍት አድርጎት ስለነበረ በመላው ዓለም ያሉ ሁሉ ይቀባበሉታል። ከዚህ ቅብብሎሽ በኋላም እስከ አሁን ድረስ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎች በልደት ዝግጅቱ ላይ እንደሚገኙ የማረጋገጫ መልዕክት ለአቶ ኢባራ ልከዋል። በዚህ ምላሽም አቶ ኢባራ እጅግ ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል።

ስለሁኔታው መረጃ የደረሰው የሀገሪቱ ፖሊስ መምሪያ ይህ ሁሉ ህዝብ በሚሰበሰብበት ወቅት ያልተፈለገ ድርጊት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት የፖሊስ ሃይል ሊመደብ ተሰማምቷል። ድንገት አደጋ ቢያጋጥም የሰዎችን ህይወት ማትረፍ እንዲቻልም የቀይ መስቀል ሰራተኞች በከተማዋ እንዲገኙ ተወስኗል። የከተማዋ አየር መንገድም በቅርብ ርቀት ላይ ላሉ እና በልደት ዝግጁቱ ላይ ለመሳተፍ ወደ ከተማዋ ለሚመጡ ሰዎች የ30 በመቶ ቅናሽ እንደሚያደርግ ተናግሯል። በልደት ዝግጅቱ ላይ ለሚገኙ ታዳሚዎች ሶስት የሙዚቃ ባንዶች ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ በተጨማሪም የፈረስ ግልቢያ ውድድር እንደሚኖር ተገልጿል። እንደተባለው ይህን ያህል ቁጥር ያለው ህዝብ በልደት ዝግጅቱ ላይ መገኘት ከቻለ ምናልባትም የሩቢ ኢባራ ጋርሲያ ልደት የመጀመሪያው በበርካታ ሰዎች የተከበረ ልደት ሊሆን ይችላል። በሁኔታው ክፉኛ ግራ የተጋባው አቶ ኢባራ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ቃል “በአቅራቢያችን ያሉ ሰዎች በዝግጅቱ ላይ እንዲገኙ መጋበዝ ፈልገን ነበር። ነገሩ ይኸው ነው” ከማለት ውጪ ተጨማሪ አስተያየት መስጠት አልቻሉም። የተለያዩ ኮሜዲያን ግን እየቀለዱበት እና እያፌዙበት ነው ሲል ዜናውን ሚረር ኦንላይን ነው። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
396 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 934 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us