የዓማችን መለሎ ውሻ

Wednesday, 04 January 2017 14:27

በዓለማችን ላይ በርካታ የውሻ ዝርያዎች ይስተዋላሉ። አንዳንድ ውሾች ደግሞ አጀብ የሚያሰኝ አፈጣጠር ይስተዋልባቸዋል። የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብም በዘንድሮ እትሙ የዓለማችን መለሎ ውሻ ብሎ የመዘገበውን ውሻ እናስተዋውቃችሁ። ይህ ውሻ ስሙ ፍሬዲ ሲሆን፤ የተገኘውም ከእንግሊዝ ነው። ፍሬዲ በኋላ እግሩ ሲቆም ርዝመቱ ሰባት ጫማ ከስድስት ኢንች ነው። በዚህ ቁመቱም የዓማችን መለሎው ውሻ ተብሎ ስሙን በመዝገቡ ላይ አስፍሯል። የፍሬዲ አሳዳጊ የሆነችው ክላሪ ስቶንማን ፍሬዲን ገና ቡችላ ሳለ እንዳገኘችው ትናገራለች። ፍሬዲ ፍሎር የተባለች እህት እንዳለችው የተናገረችው ስቶንማን፤ እድገቱም ሆነ የቁመቱ እርዝመት ከእህቱ የበለጠበት መንገድ በእርሷም አስደናቂ መሆኑን ትናገራለች። ወደቤቷ ስታመጣው ከእህቱ በግማሽ ያህል ቁመቱ ያጥር እንደነበር ያስታወሰችው አሳዳጊው፤ ነገር ግን በሳምንት 123 ዶላር ወጪ እያደረገች የተጠበሰ ዶሮ እና የኦቾሎኒ ቅቤ ስትመግበው እንደቆየች ትናገራለች። መጀመሪያ ላይ ስቶንማን ፍሬዲን ወደቤቷ የወሰደችው ህይወቱን ለማትረፍ አስባ እንደነበር የገለፀች ሲሆን፤ በዚህ መልኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና በማግኘቱ መደነቋን ለቢቢሲ ገልጻለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
408 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 120 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us