ከዓለማችን ጦር ሠራዊት አልባ ሀገራት በጥቂቱ

Wednesday, 04 January 2017 14:28

የአንድ ሀገር ጥንካሬ የሚለካው በጦር ሰራዊቱ ጥንካሬ ነው። በዚህም ሳቢያ ሁሉም ሀገራት አንዱ ከሌላው የላቀ እና የጠነከረ የጦር ሰራዊት እንዲኖራቸው የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ያደርጋሉ። ከዚህ በተቃራኒው ግን የራሳቸው የሆነ የጦር ሠራዊት ወይም የጦር ኃይል የሌላቸው ሀገራት እንዳሉ ያውቁ ኖሯል? በዓለማችን ላይ ካሉ ጥቂት የጦር ኃይል ወይም የጦር ሰራዊት አልባ ከሆኑት ሀገራት የሚከተሉት ይገኙበታል።

አንዶራ፡- ይህች ሀገር ምንም የራሷ የጦር ኃይል የሌላት የዓለማችን ሀገር ናት። በሀገሪቱ ህግና ደንቦች እንዲሁም በፓርላማ የሚፀድቁ ኃላፊነቶች የሚተገበሩት በፖሊስ ነው። ሀገሪቱን ከጥቃት እና ከወረራ የመከላከል ኃላፊነቱ የተሰጠውም በድንበር ለሚያዋስኗት ስፔን እና ፈረንሳይ ጦር ኃይሎች ነው። በሀገሪቱ ጥቂት ቁጥር ያላቸው የጦር ሠራዊት ያሉ ቢሆንም የእነዚህ ሠራዊት መኖር ህግና ደንብን ለማስከበር ሣይሆን ለወግ እና ለክብረ በዓል ማድመቂያ የሚውል ብቻ ነው።

ኮስታሪካ፡- ኮስታሪካ እ.ኤ.አ. ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ የራሷ የሆነ የጦር ሰራዊት የላትም። ይህች ሀገር በ1948 ዓ.ም በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቃ የነበረ ሲሆን፤ ይህን ጦርነት ተከትሎም በሀገሪቱ የጦር ሠራዊት እንዳይኖር ተደረገ። ይህች ሀገር የራሷ የጦር ሰራዊት የሌላት የዓለማችን ትልቋ ሀገርም ናት። የሀገሪቱ የውስጥ የፀጥታ ጉዳይ በፖሊስ የሚተዳደር ሲሆን፣ ምንም እንኳን ሀገሪቱ ከኒካራጓይ ጋር በየጊዜው የድንበር ግጭት ውስጥ ብትገባም አሁንም ድረስ ግን የራሷ የጦር ሠራዊት የላትም።

ዶሚኒካ፡- ዶሚኒካ ከ1981 (እ.ኤ.አ.) ዓ.ም ጀምሮ የራሷ የሆነ የጦር ሠራዊት የሌላት ሀገር ናት። ሀገሪቱ የጦር ሰራዊት እንዳይኖራት የተደረገውም በአንድ ወቅት ከፍተኛ መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደባት በኋላ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ልክ ከላይ እንደተጠቀሱት ሀገራት ሁሉ የሀገር ውስጥ ፀጥታ ጉዳይ በፖሊስ ይተዳደራል።

ሐይቲ፡- ይህች ሀገር እ.ኤ.አ. ከ1995 ዓ.ም ወዲህ ነው የራሷ የሆነ የጦር ሰራዊት የሌላት። በሀይቲ በርካታ መፈንቅለ መንግስቶች እና በርካታ የውስጥ ግጭቶች በተደጋጋሚ መከሰታቸው ነበር መንግስት የጦር ሠራዊቱን እንዲበትን ያስገደደው። የጦር ሠራዊቱ በተደጋጋሚ በመንግስት ላይ በማመፅ መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ ሀገሪቱ የጦር ሠራዊት አያስፈልገኝም ብላ በትናዋለች። እስከ አሁን ድረስም በዚህ አቋሟ እንደጸናች ትገኛለች።

አይስላንድ፡- ይህች ሀገር እ.ኤ.አ ከ1869 ዓ.ም ጀምሮ የጦር ሠራዊት የላትም። ይህች ሀገር ለዚህ ሁሉ ዓመት (1481 ዓመታት) ያለ ጦር ሠራዊት መቆየቷ ብቻ አይደለም የሚያስገርመው። ሀገሪቱ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) አባል ሀገር መሆኗም ጭምር ነው። ምንም እንኳን ሀገሪቱ የራሷ የሆነ የጦር ሰራዊት ባይኖራትም ከአሜሪካ ጋር ግን የመከላከያ ስምምነት አላት።

ሞሪሺየስ፡- ሞሪሺየስ ከአውሮፓዊያኑ 1968 ዓ.ም ጀምሮ ቋሚ የሆነ የራሷ የጦር ሠራዊት የላትም። ሀገሪቱ ለዚህ ማካካሻ ይመስላል ጠንካራ የፖሊስ ኃይል አላት። በሀገሪቱ 10ሺህ ያህል ንቁ የፖሊስ ኃይል የሚገኝ ሲሆን፤ ይህ የፖሊስ ኃይልም የጦር ኃይል ጉዳይ ሙሉ ለሙሉ፣ የፖሊስ ጉዳይ እንዲሁም የሀገሪቱ የፀጥታ ጉዳይ የሚመለከተው ይሄንን የፖሊስ ኃይል ነው። የፖሊስ ኃይሉም በፖሊስ ኮሚሽን ትዕዛዝ የሚተዳደር ነው።

የሰለሞን ደሴቶች፡- ይህች ሀገር ቀደም ሲል የራሷ የሆነ የጦር ሠራዊት ነበራት። ነገር ግን በሀገሪቱ የተከሰተውን ከፍተኛ የብሔር ግጭት ተከትሎ ግን የጦር ሰራዊት ይቅርብኝ ብላለች። በብሔር ግጭቱ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ በመሆናቸው የሀገሪቱ ጦር ሠራዊት እንዲበተን ተደርጓል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ሀገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የፖሊስ ኃይል ውስጣዊ የፀጥታ ጉዳዩዋን ትቆጣጠራለች።

ሞናኮ፡- ሞናኮ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያለ ጦር ሠራዊት ነው ያለችው። በሀገሪቱ ቋሚ የሆነ የጦር ሠራዊት ባይኖም ሁለት ንኡስ የጦር ኃይሎች አሉ። አንደኛው የጦር ኃይል የሀገሪቱን ልዑል የሚጠብቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ሲቪሎችን የሚጠብቅ ነው። የሀገሪቱን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለባት ግን ፈረንሳይ ናት። 

ይምረጡ
(4 ሰዎች መርጠዋል)
1168 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 121 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us