ግብረ ይሁዳ

Wednesday, 11 January 2017 14:03

 

እግዜር ሆይ -

ያው ያንተን አላውቅም

እንኳን ያንተን ሁልቆ - የራሴንም ደቂቅ - ቆጥሬ አልዘልቅም

(ግን ህዝብህ ቆሳስሎ . . .)

ባለ ንጨት ቀዳሾች - በቤትህ ቢገኑ -ማየቱ አይጨንቅም?

ዘመኑ ድፍርስ ነው - ምንም የማይጠራ

ለጠያቂው ህመም - ለመላሹም ግራ፣

ስምህን የጠራ - “የቤትህ ጠበቃ” - ሸር ነው ቀለቡ

“የካደህ ይሁዳ” - ለድሆች ያለቅሳል - ገራገር ነው ልቡ

ይህንን ግልብጥብጥ - ትመልስለት ዘንድ - አንተን ያያል ህዝቡ፣

ምን ትላለህ አንተ?

ሀይማኖት ሲዋለድ - ፍቅር እንዴት ሞተ?

ከቀዳሾችህ ልብ - የድሆችን ለቅሶ - ማነው የጎተተ?

እግዚር ሆይ አደራ

አንተም እንደ ነሱ - ጥያቄ ለማምለጥ - ሰይጣንን አትጥራ

“ለሰበብ አስባቡ - መልስ ነኝ. . .” እያለ - እሱም እንዳይኮራ።

“ሃይማኖቴን” እንጂ - “እምነቴን” የሚሉ

ከቤትህ ሲሸሹ - ከቤትህ ሲጎሉ. . .

የትኛው ግድ አለው? - ማነው ዞሮ ያየ?

ማንስ ሀይማኖቱን - ከእምነቱ ለየ?

ቆይ . . . ቆይ . . . ቆ . . ይ. . .

በተራበ ቤትህ - ማን ሆዳምን ሾሞ - የዋሆችን ሻረ?

(ከሚክዱት ይልቅ. . .­)

ክፉ “ፃድቅ” ሾሞ - በቋፍ ያለን አማኝ - ማን አደናገረ?

“. . . እግዜር የበላይ ነው . . . ሿሚና ሻሪ ነው. . .” - ተብዬ ነበረ. . .

ነገሩን ነው እንጂ . .  ችግር የለም ኧረ. . .

እኔን የቸገረኝ . .  መገለባበጡ

“ከሀዲው” ሲሰራ. . “እማኝ” መበጥበጡ

“ኃጥእ” እየረጋ . .  “ፃድቅ” መራገጡ!!!

ሀይማኖቴ ባዩ - እውነትህን ሸሽቶ - ህዝብህን ይፈጃል

“ኢ -አማኝ” ያን አይቶ - አማኞችን ሁሉ - በአንድ ይፈርጃል

እና ምን ይበጃል?

ያው ቅድም እንዳልኩህ - ካ'ንተ አላ'ቅም እኔ. . .

ግራ ቢገባኝ ነው - ታማሚው ዘመኔ

(“አምንሃለሁ.  . .” ያለህ.  . .)

በአፉ “ሲቀደስ” - ግብሩ ግን ሲጠቃ - በትዕዛዝህ ጠኔ!

                                        ፍርድ እና እርድ - አበረ አያሌው

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
429 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 163 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us