የ105 ዓመቱ ባለክብረወሰን

Wednesday, 11 January 2017 14:12

ዕድሜ ሲገፋ እጅና እግርን አጣጥፎ ከመቀመጥ ይልቅ ነገሮችን በተቻለ አቅም ሁሉ የመሞከር ጉጉት ያድራል። ከወደፈረንሳይ ሰሞኑን የተሰማው ዜና የሚነግረን ደግሞ ለእርጅና እጅ አልሰጥም ያሉት የዕድሜ ባለፀጋ የዓለም ክብረወሰን መስበራቸውን ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው። ፈረንሳዊው የዕድሜ ባለፀጋ ሮበርት ማርቻንድ እድሜያቸው 105 ዓመት ነው። ቀድሞም በብስክሌት ግልቢያ የሚታወቁት አቶ ማርቻንድ ከሰሞኑ 14 ማይልስ ርቀትን በአንድ ሰዓት ውስጥ በብስክሌት በመጋለብ ክብረወሰንን ሰብረዋል። በሴንት ኩዌንቲን አደባባይ ተሰብስበው በነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አድናቂዎቻቸው ፊት ለፊት ፉክክራቸውን ያደረጉት አቶ ማርቻንድ 92 ዙሮችን በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ ፉት ብለዋታል ሲል የዘገባው ዘጋርዲያን ነው። አዛውንቱ ማርቻንድ እንዲህ አይነቱን ድል ሲያጣጥሙ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ቀደም በርካታ ክብረወሰኖችን በብስክሌት ግልቢያ አሻሽለዋል። ከአንድ መቶ በላይ በሆኑ የብስክሌት ግልቢያ አይነቶች ለበርካታ ጊዜ ስማቸው ተጠርቷል። 16 ማይልስ ርቀትን በአንድ ሰዓት ውስጥ በመጋለብ የራሳቸው የሆነ ክብረወሰንን መያዝም ችለዋል። አሁን ደግሞ ብዙዎች ለጡረታ እና ለእርዳታ እጃቸውን በሚዘረጉበት እድሜ ላይ ሆነው አዲሱን ክብረወሰን አስመዝግበዋል።

አቶ ማርቻንድ አደርገዋለሁ ብለው ከተነሱ ሃሳባቸውን ሳያሳኩ ወደኋላ እንደማያፈገፍጉ አሰልጣኛቸው ጭምር መስክረውላቸዋል። ለሚያደርጓቸው ነገሮችም ሰፋ ያለ ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ። ይሄንን ክብረወሰን ለመስበር ሲወስኑም አስቀድሞ ወደ አትክልት በልነት ተቀይረው ነበር። ከውድድሩ አንድ ወር ቀደም ብለው ጀምሮ ምግባቸውን አትክልት ብቻ ያደረጉ ሲሆን፤ ዶክተሮች ግን የስጋ ተዋፅኦ በምግባቸው ውስጥ እንዲያካትቱ አበረታትተዋቸዋል። “ሰውነታቸው ሲታይ አነስተኛ እና ኮሳሳ ይመስላሉ። ልባቸው ግን ትልቅ ነው። በሰውነታቸው ላይ ያለው ኃይልም ከእርሳቸው ዕድሜ በግማሽ ላይ ያለ ነገር ግን ስፖርት ከማይሰራ ሰው እኩል ነው” ሲሉ አንድ ባለሙያ አስተያየት ሰጥተዋል።

አቶ ማርቻንድ በዚህ እድሜያቸው ማልደው ከእንቅልፋቸው ይነሳሉ። ለአስር ደቂቃ ያህል ሰውነታቸውን ለማጠንከር እና ቅርፃቸውን ለመጠበቅ የሚያግዛቸውን ስፖርት ይሰራሉ። በቤታቸው ውስጥ ቀጥሎም ከቤታቸው ውጪ የስፖርት ልምምድ ከጓደኞቻቸው ጋር ማድረግም ዋናው ስራቸው ነው። ይሄንን በሳምንት አራት ጊዜ ያደርጉታል። ይሄ ታዲያ የየእለት ተግባራቸው ብቻ መሆኑን ይናገራሉ። “እነዚህ ነገሮች የማደርገው ክብረወሰን ለመስበር አይደለም። ይልቁንም በ105 ዓመት እድሜ ላይ ሆኖ ብስክሌት መጋለብ እንደሚቻል ለማረጋገጥ ነው” ሲሉ አቶ ማርቻንድ አዲሱን ሪከርድ ከመስበራቸው አስቀድመው ተናግረዋል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
421 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1038 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us