ማ?

Wednesday, 18 January 2017 10:06

 

የኔ እናት

ፍርፋሪ እንዳማራት፣

ኃምሮቷ ሳይቆርጥላት፤

ማስመለስ ቁርጠቱን፤

ውጋት እና እብጠቱን፤

ዘጠኝ ወር ታግሳ፤

መሬት ላይ ተንቆራጣ፤

ሙሉ ቀን አምጣ፤

ዓይኗን በዓይኗ አለየች።

ጡቷ ቆረንጮ እስኪሆን አገጥግጣ፤

ሽንት እና ሰገራ ተቀብላ በፎጣ፤

ወደ ላይ፣ ወደ ላይ አዘልላ አጫውታ፤

በጀርባዋ አዝላ ወቀጣ ፈጭታ፤

አሳደገች በአጽሟ ሄዳ ተንገላታ።

እኔ እናቴን ስጠራት፤

“እናት ዓለም፤ እማምዬ” ነው የምላት።

የልጄ እናት

የሷ አማረኝ፤

ሳያማርረኝ፤

ክትፎ፣ በርገር፣ ፒዛ

ሁሉ እየተገዛ፤

ሲቆርጣት ሲወጋት፤

ዶክተር ሳይለያት፤

ዘጠኝ ወር ታግሳ፤

ወለደች በቤሳ።

ከልጇ መፋፋት ውበትን መረጠች፤

ለጡቷ ማስያዣ ለልጅ ጡጦ ሰጠች፤

ሽንትና ሰገራን በዳይፐር አፈነች፤

አዛይ እና አጫዋች ሞግዚቷን ቀጠረች።

ልጄ እናቱ እና ሞግዚቱ ስለተምታቱበት፤

“ማ?” ብሎ ይቀራል እናቱን ሲጠራት።

“ሚን” አይጨምራትም፤

ምክንያቱም፤

እንዴት ሙሉ ሳትሆን “ማሚ” ብሎ ይጥራት፤

የግማሽ እናቱ “ሚ” የሞግዚቷ ናት።

            ምስጢረ ውሃነት - ደረጃ ዳኜ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
440 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1013 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us