በዳንሰኞች የታጀበው ቀብር

Wednesday, 25 January 2017 13:03

 

ሞት ለማንም የሰው ልጅ የማይቀር የህይወት አንዱ አካል ቢሆንም በአንዱ ላይ ሲከሰት ቋሚን ለሀዘን ይዳርገዋል።  በአብዛኛው ሞትን ተከትሎ የሚከናወኑ ስርዓተ ቀብሮች በዘመድ ወዳጅ ሀዘንና ለቅሶ የሚደመደሙ ናቸው።  ሆኖም ግን በዓለማችን ላይ ባሉ አንዳንድ ሀገራት የሙታን ስርዓተ ቀብር ለየት ባለ እና በሀዘን ሳይሆን በደስታ ድባብ ሲከናወን ይታያል።  ለዚህ ማሳያ የሚሆን እና የዓለምን ጆሮ ስቦ የነበረ አንድ ክስተት ከሰሞኑ ከወደ ታይዋን ተሰምቷል።

ነገሩ እንዲህ ነው።  ቱንግ ያንግ በሀገረ ታይዋን ቀደም ባለው ጊዜ ታዋቂ ፖለቲከኛ ነበሩ።  በአሁኑ ወቅት ከፖለቲካው አለም ራሳቸውን አግልለው ህይወታቸውን በመምራት ላይ ሳሉ የማይቀረው ሞት ጎበኛቸው።  እናም የዚህች አለም የ76 ዓመታት ኮንትራታቸውን አጠናቀው ተሰናበቱ።  መሞታቸውን ተከትሎ የተከናወነው ስርዓተ ቀብራቸው ታዲያ የዓለምን ትኩረት ስቦ ሰንብቷል።  የአቶ ያንግ ስርዓተ ቀብር የተፈፀመው በ50 የፖል ዳሰኞ ታጅቦ ነበር።  በሀገሪቱ አሉ የተባለ 50 ዘመናዊ የፖል ዳንሰኞች አስክሬኑን አጅበው ትርኢታቸውን እንዲያቀርቡ ተደርጓል።  በሂል ጫማዎች ላይ ቆመው በአጭር ቲሸርት እና የውስጥ ሱሪዎች ተመሳሳይ አለባበስ የቀረቡት ዳንሰኞቹ በተለያየ ቀለም ባላቸው ጂፕ ተሸከርካሪዎች ላይ በተዘጋላቸው ብረት ላይ ወጥተው ትርኢታቸውን አቅርበዋል።  ትርኢቱም ሁለት ሰዓታትን የፈጀ ነበር።

የአባቱ ስርዓተ ቀብር በዚህ መልኩ እንዲከናወን ቅድመ ዝግጅቱን ያመቻቸው የሟጅ ልጅ ስለሁኔታው ሲጠየቅ በሰጠው ምላሽም አባቱ በህልሙ ታይተውት ይሄ ነገር እንዲደረግላቸው መናገራቸውን ገልጿል።  አቶ ያንግ ሲሞቱ ስርዓተ ቀብራቸው እንደ ለቅሶ ሳይሆን እንደሰርግ ለየት ባለ መልኩ እንዲከናወን ፅኑ ፍላጎት እንዳላቸው በህልሙ እንደታየውም ልጃቸው ተናግሯል።  የአባቱን ፍላጎት የመፈጸም እና በህልሙ ያየውን ነገር የማክበር ኃላፊነት ያለበት ልጅም አባቱን ያስደስታል ባለው መልኩ ማስፈፀሙን ለሮይተርስ ገልጿል።  በትርኢቱ ላይ ከበሮ ደላቂዎች፣ ሰንደቅ ዓላማ አውለብላቢዎች እና ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችም ተሳታፊ ነበሩ ተብሏል።  

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
434 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 950 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us