“እንቆቅልሽ. . .”

Wednesday, 01 February 2017 13:36

 

ድሪቶ የለበሰች፤ አንድ እማ ኮታታ

ባደፈ ቀሚስ ላይ፤ ኩታዋን አጣፍታ

ፊቷና ቀሚስዋ፤ የተመሳሰሉ

ተጥፈው ተጣጥፈው፤ ታሪክን የሳሉ

ሃሳብና ገፅዋ፤ አንዳች የማይገጥሙ

ጆሮቿ ሩቅ እንጂ፤ ከቅርብ የማይሰሙ

አይኖቿ ታውረው፤ አድማስ ’ሚያልሙ

ዛሬን ረግጣ ነገን፤ የተንጠላጠለች

በነገ ዛሬ አለ፤ ልታገስ እያለች

ሙት ኑዋሪዎችን፤ መስላ ትኖራለች

እቺ እማ ኮተቴ፤ 10 ልጆች አልዋት

ድህነቱዋን ንቀው፤ ’ዞር በይ’ የማይልዋት

አንዱ ልጅዋን ጉሊት፤ ሁለቱን ቀንስራ

ሁለቱን አስኩዋላ፤ አንዱን ዶሮ ተራ

ሁሉን በየአቅጣጫው፤ ለኑሮ ዘርዝራ

እሱዋ ከጎጆዋ፤ ትውላለች ባክና

እግሯን ላታነሳ፤ ላትርቅ ወስና

በየቀኖች መሀል፤ ትደናበራለች

ኮሽታ ስትሰማ፤ ክፉ ትፈራለች

ድንገት ሰው ሲንጫጫ፤ መንደሩ ይናጋል

የማ ኮተት ጆሮም፤ ከማጀት ይሰጋል

እግሯን ሳታነሳ፤ ከጎሬዋ እንዳለች

ትንፋሽዋን ዋጥ አርጋ፤ ጆሮ ትጥላለች

አጥፊና ጠፊ ላይ፤ እዛው ትፈርዳለች

እንዳንዴም፤

ኡኡታው ሲበዛ፤ ሲሸበር መንደሩ

የሷም ቤት ይጮሃል፤ ይከፈታል በሩ

ባደፈ መቀነት፤ ወገብዋን ሸብ አርጋ

መሀል ትሰፍራለች፤ ነገር ልታረጋ

ጎረቤት ሲታመስ፤ እያለች ነግበኔ

በልጆቿ ተስፋ፤ በታጠረ ወኔ

እዚያም ዘው እዚያም ዘው በደከመ ክርኗ

በጥድፊያ እርጋታ ባረጀ ዘመኗ

ዘመን ያልጎበኛት መታያ ያልሆናት

በሉ ተጠየቁ ይች አሮጊት ማናት?

            እንዴት ብሎ - በስመኝ ታደሰ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
360 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 942 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us