ብርቱዎቹ አፍሪካዊያን ሴቶች

Wednesday, 01 February 2017 13:39

 

ጆይሲ ባንዳ

እኚህ ሴት የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ነበሩ። በፕሬዝዳንትነት ዘመናቸውም ሙስናን በመዋጋት፣ ወላጆቸውን ላጡ ህፃናት እርዳታ የሚያደርጉ ተቋማትን በማስፋፋት፣ ለሴቶች ብልጽግና በመስራት እና ረሃብን ለማጥፋት ባደረጓቸው መልካም ተግባራት ይታወቃሉ። ባንዳ  በስልጣን ዘመናቸው 15 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የፕሬዝዳንት ጀቶችን በመሸጥ የቅንጦት አኗኗርን በማስቀረት፣ ደመወዛቸውን 30 በመቶ በመቀነስ እንዲሁም ለሙስና ተጋልጧል ያሉትን ኮሚቴ ሙሉ ለሙሉ በማፍረስ ሙስናን ለማጥፋት በስፋት ሰርተዋል።

­

ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ

ሰርሊፍ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ፤ በአፍሪካም የመጀመሪያዋ የሀገር መሪ ናቸው። ሰርሊፍ ለፕሬዝዳንትነት ስልጣን ሁለት ጊዜ የተመረጡ ሲሆን ከ2005 እስከ 2011 የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል። በስልጣን ዘመናቸውም ብሔራዊ እዳን በመቀነስ፣ ብሔራዊ አንድነትን በማበረታታት፣ ጠንካራ ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በማበረታታት እንዲሁም ለትምህርት እና ለጤና አጠባበቅ ቅድሚያ በመስጠት ይታወቃሉ። በዚህ ተግባራቸውም በ2011 የሰላም ኖቤል ፕራይዝ ተሸላሚ ሆነዋል።

­­­

ሳሚያ ሀሰን

ሳሚያ ሱላሉ ሀሰን የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ የመጀመሪያዋ ሴት ናቸው። እኚህ ሴት ይህ ብቻም ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካም ከዩጋንዳም ስቼሊዮሳ ዋንዲራ ቀጥለው ሁለተኛዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው። ሳሚያ የማስንዱቺ ፓርላማ አባል ሆነውም አገልግለዋል። በዛንዚባር በሰራተኛ፣ ስነፆታ እና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስትርነት፣ በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ሚኒስትርነት እንዲሁም በታንዛኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርነት አገልግለዋል።

ጆይስ ሙጁሩ

የዚምባቡዌ ተወላጇ ሙጁሩ የሀገሪቱ የመጀመሪያዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በ2004 ተሸመዋል። እኚህ ሴት በሀገሪቱ የወጣቶች፣ ስፖርትና መዝናኛ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙ በእድሜ ትንሿ ሴትም ነበሩ። ሙጁሩ ይሄ ብቻም ሳይሆን፤ በአፍሪካ ናሽናል ሊብሬሽን አርሚ የመጀመሪያዋ ሴት ኮማንደር ናቸው። ሙጁሩ በበርካታ ጦርነቶች ላይም የተሰማሩ ሴት ናቸው።

ድላሚኒ ዙማ

ኒኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ በዚህ ሰሞን ለተተኪ ያስረከቡት የአፍሪካ ህብረት ዋና ፀሐፊ ናቸው። እኚህ ሴት በደቡብ አፍሪካ ፖለቲካ ውስጥ ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል። በአፍሪካ ህብረት ፀሐፊነት የተመረጡ ብቸኛዋና የመጀመሪያዋ ሴት ሲሆኑ፤ የነጻነት፣ የህብረት እንዲሁም ሴቶችን የማብቃት አቀንቃኝ ናቸው።

ማርታ ካሩዋ

ማርታ በኬንያ ፖለቲካ ውስጥ አሻራቸውን ያሳረፉ ሴት ናቸው። እኚህ ሴት የህግ ባለሞያ ሲሆኑ፣ ከምስራቅ አፍሪካም ፈር ቀዳጅ ሕግ አውጪዎች አንዷ ናቸው። በሀገራቸው ኬንያ የቤተሰብ ሕግ እንዲፀድቅ በማድረግ ረገድም ቀዳሚዋ ሴት ናቸው። እኚህ ሴት ብረቷ ሴት (The iron lady) በሚል ቅፅል ስምም ይታወቃሉ። ማርታ በሀገራቸው በተለያዩ የሚኒስትርነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥም የውሃ ሀብት ማኔጅመንት እና ልማት ሚኒስትር፣ የፍትህ ሚኒስትር እንዲሁም የህገ መንግስት ጉዳዮች ሚኒስትርም ሆነ አገልግለዋል።

የቻይናዋ ከተማ መልካም ተሞክሮ

የቻይናዋ ዢያን ሲቲ ሰሞኑን አንድ ለዓለማችን አዲስ የሆነ ነገር መተግበር ጀምራለች። ከተማዋ ያደረገችው ነገር በሌሎች ሀገራትም ቢለመድ ጥሩ ነውና እናካፍላችሁ። ቢቢሲ የዜና አውታር ሰሞኑን የከተማዋን ሻንግ ባኦ ጋዜጣ ጠቅሶ እንደዘገበው በዢያን ከተማ በሚገኙ መፀዳጃ ቤቶች አቅራቢያ በርካታ ነፃ የመኪና ማቆሚያዎችን አዘጋጅታለች። እነዚህ የመኪና ማቆሚያዎችም የተፈጥሮን ጥያቄ ለመመለስ ለሚፈልጉ ባለሙያዎች ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው። በእነዚህ በሀገሪቱ ዋና ጎዳና አካባቢ የተዘጋጁት የመኪና ማቆሚያዎች አቅራቢያ 50 የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች አሉ። አንድ ሰው በእነዚህ ቦታዎች ላይ መኪናውን አቁሞ ወደ መፀዳጃ ቤቶቹ ሲያመራም የሚሰጠው የመቆያ ጊዜ 15 ደቂቃ ነው። ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሞ መኪናውን በማቆም እቃ ለመግዛት ወይም ለሌላ ስራ የሚሄድ ሰው ካለም በቦታው ላይ የተሰማሰሩ የትራፊክ ፖሊሶች ቅጣት ይጥሉበታል። ከዚህ አገልግሎት ውጪ ለሆነ አገልግሎት ብለው መኪና የሚያቆሙ ሰዎችም ለቅጣት ይዳረጋሉ ተብሏል። ዢያን ከተማ ከ1ሺህ 300 በላይ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ስላሏት በቀጣይም የከተማዋ ትራፊክ ፖሊሶች ተመሳሳይ የመኪና ማቆሚያዎችን በማመቻቸት በርካታ ሰዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ሲል ዘገባው አስነብቧል።   

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
449 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1040 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us