ውድቅዳቂዎች ለክፍያ እየዋሉ ነው

Wednesday, 08 February 2017 14:47

 

ከወደ ቤላሩስ ሰሞኑን አንድ አስገራሚ ዜና ተሰምቷል። በከተማዋ ደቡባዊ ግዛት የሚገኘው ምክር ቤት የአካባቢዋ ዜጎች ለአንዳንድ አገልግሎቶች ውድቅዳቂ እቃዎችን እንደክፍያ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል። ነዋሪዎቹ ለውሃ እና ለነዳጅ አገልግሎት ክፍያ መክፈል ሲፈልጉ አገልግሎት ላይ የዋሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን፣ ወረቀቶችን እንዲሁም አሮጌ መስታወቶችን እንደ ክፍያ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል። ይሄን ውሳኔ ለመወሰን የተገደዱትም ዜጎች ወጪያቸውን በገንዘብ መክፍል እያቃታቸው በመምጣቱ እንደሆነ ተዘግቧል።

ዜጎች ይህን አገልግሎት መጠቀም እንዲችሉ በተለያዩ በራሪ ወረቀቶች ማስታወቂያ እየተላለፈ መሆኑ ተገልጿል። የምክር ቤቱን ውሳኔ ለዜጎች እንደ እርዳታ የቆጠሩት በርካቶች በደስታ የተቀበሉት ሲሆን፣ አንዳንዶች ግን ጥርጣሬ ገብቷቸዋል። በተለይ ለምን ያህል እዳ ምን ያህል እቃ መሰጠት እንዳለበት በግልፅ የተቀመጠ ነገር ባለመኖሩ ግራ ያጋባቸው ሰዎች አሉ። አንዳንዶቹም እነዚህን ጥቅም ላይ የዋሉ እቃዎች አሰባሰቦ በውድ ዋጋ ለመሸጥ የታሰበ ብልሃት ነው ሲሉ ሲነቅፉት ተሰምተዋል። ያም ሆነ ይህ የግዛቲቱ ዜጎች ለውሃና ለነዳጅ ወጪ መሸፈኛ የሚያስፈልጋቸው ገንዘብ ሳይሆን አገልግሎት ላይ የዋሉ የፕላስቲክ ጠርሙሶች፣ ወረቀቶች እና መስታወቶች በመሆናቸው ያለ ስጋት መገበያየት ተፈቅዶላቸዋል ሲል ያስነበበው ቢቢሲ የዜና አውታር ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
294 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 947 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us