ድብቁ ጎራዴ

Wednesday, 15 February 2017 13:18

 

የ80 ዓመቷ ዕድሜ ባለፀጋ ሀገር አማን ብለው ያሰቡት ቦታ ለመድረስ ወደ አሜሪካው አየር መንገድ ያመራሉ። እድሜ አቅም የነሳቻቸው እኚህ የ80 ዓመት እናት ብርታት ይሰጣቸው ዘንድ በከዘራቸው እየታገዙ ነው የሚጓዙት። ወደ አየር መንገዱ የፀጥታ ቁጥጥር ግዛት ሲገቡ ግን ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው። በፀጥታ ቁጥጥር ጣቢያው ውስጥ ያሉት ተቆጣጣሪዎች እኚህ ሴት የያዙትን ከዘራ ደጋግመው ራጅ አነሱት። የራጁ ውጤት ያመለከተው ነገር ሌላውን ሰው ብቻም ሳይሆን የእድሜ ባለፀጋዋንም ግርምት ፈጠረባቸው። በምርመራው ማረጋገጥ የተቻለው በአዛውንቷ ከዘራ ውስጥ ጎራዴ መኖሩ ነው።

የአየር መንገዱ ፀጥታ ቁጥጥር ቃል አቀባይ ማርክ ሆዌል እንደገለፁት ከዘራው በራጅ ማሽን እንዲነሳ ሲደረግ በከዘራው ውስጥ የተጠማዘዘ እና የተለጠጠ ጎራዴ ተገኝቷል። ሴትየዋ ነገሩን ሲሰሙ እስከዛሬ ድረስ በከዘራቸው ውስጥ ጎራዴ ስለመኖሩ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው እና እርሳቸውም በዜናው መደናገጣቸውን ተናግረዋል። የእድሜ ባለፀጋዋ እንደተናገሩትም ከዘራውን ከልጃቸው በስጦታ መልክ ያገኙት ሲሆን፣ በውስጡ ስላለው ነገር ምንም ሳያውቁ ለዓመታት ሲጠቀሙበት እንደቆዩ ገልጸዋል። አየር መንገዱም በእድሜ ባለፀጋዋ ከዘራ ውስጥ የተገኘው ጎራዴ ከጦር መሳሪያ ተርታ የሚመደብ በመሆኑ በአውሮፕላን መጓጓዝ አይችልም በሚል በቁጥጥር ስር በማዋል ሴትየዋ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ አድርጓል ሲል ያስነበበው ዩናትድ ፕሬስ ኢንትርናሽናል ነው።  

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
446 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 947 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us