አስቂኝ የዓለማችን ህጎች

Wednesday, 15 February 2017 13:19

 

በዓለማችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ነገስታት እና ሀገር ገዢዎች የየራሳቸውን ህግጋት በማውጣት ህዝባቸውን ለማስተዳደር ይሞክራሉ። ህግጋቱ እንደየጊዜው ሁኔታ ትክክለኛ መስለው ቢታዩም በሌላ ወቅት ደግሞ አስቂኝ፣ አስገራሚ እንዲሁም አነጋጋሪ የሚሆኑበት ሁኔታ ይኖራል። እስኪ በአንድ ወቅት የነበሩ ምናልባትም አሁንም ድረስ እየተተገበሩ ሊሆኑ የሚችሉ የዓለማችን አንዳድ ህግጋትን እንጥቀስ።

-    በአሪዞና ሞሔቭ ግዛት አንድ ሰው ሳሙና ሰርቆ ቢያዝ ሳሙናው እስከሚያልቅ ድረስ እንዲታጠብበት ይደርገ ነበር።

-    በሚኒኦፖሊስ ህግ መሠረት ተሸከርካሪ ደርቦ ያቆመ ሰው በሰንሰለት ታስሮ ዳቦና ውሃ ብቻ እንዲሰጠው ይደረግ ነበር።

-    በሚቺጋን ህግ መሠረት የሚስት ፀጉር ባልቤትነት የባሏ ነበር።

-    በኮሎራዶ ሀገር ወንድ ልጅ በእንቅልፍ ላይ ያለችን ሴት መሳም ሕገ ወጥ ድርጊት ነው።

-    በካናዳ ኦሻዋ ግዛት ዛፍ ላይ  መውጣት ህገወጥ ድርጊት ነበር

-    በእስኮትላንድ ሕግ መሠረት አንድ ሰው በርዎን አንኳክቶ መፀዳጃ ቤትዎን ለመጠቀም ከጠየቀዎት የመፍቀድ ግዴታ አለብዎት።

-    በኦክስፎርድ ከተማ ህግ መሠረት አንዲት ሴት የወንድ ምስል ፊት ለፊት ቆማ ልብሷን ማውለቅ ያስቀጣታል፣

-    በቴክሳስ ወንጀል ለመፈፀም ያሰበ ሰው ከ24 ሰዓታት ቀደም ብሎ በቃሉ ወይም በፅሁፍ ለፖሊስ ማሳወቅ ይኖርበት ነበር፣

-    በፈረንሳይ ለአሳማ ናፖሊዮን ብሎ ስም ማውጣት በሕግ ያስቀጣ ነበር፣

-    በሚላን ከተማ ሕግ መሠረት አንድ ሰው ሁልጊዜ ፈገግ ለማለት ሕጋዊ ፈቃድ ይጠይቅ ነበር። ነገር ግን በቀብር ስነስርዓት እና በሆፒታል ጉብኝት ወቅት ፈገግ ማለት ይቻላል። ከዚህ ውጪ ፈገግ ያለ ሰው ግን ቅጣት ይጣልበታል።

-    በሩሲያዋ ቼሊያቢንስክ ከተማ ያልታጠበ ተሸከርካሪ ማሽከርከር  በህግ የተከለከለ ነው። ይህን ሕግ ተላልፎ የተገኘ ሰው ቅጣት ይጣልበታል።

-    በሐዋይ ሆኖሉሉ ከተማ ጀንበር ከጠለቀች በኋላ ድምፅን ከፍ አድርጎ መዝፈን በሕግ ያስጠይቃት።

-    በጣሊያኗ ቶሮኒቶ ከተማ ውሻን በቀን ቢያንስ ሶስት ጊዜ በእግር አለማንሸራሸር ሕግን መጣስ ነው። 

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
626 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 217 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us