ሺዎቹ የአንድ ቀን ልጆች

Wednesday, 22 February 2017 11:46

ዓለም አቀፉ የድንቃድንቅ መዝገብ በየጊዜው የሚከሰቱ አስደናቂ ክስተቶችን እየለየ ይመዘግባል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመትም የሲንጋፖር ሆስፒታል አከናውኖታል ያለውን ለየት ያለ ክስተት መዝግቧል። ኬ ኬ ኤች የተባለው የሲንጋፖር የህፃናት እና እናቶች ሆስፒታል በሆስፒታሉ በተመሳሳይ ቀን የተወለዱ ሰዎችን የማሰባሰብ ጥሪ በማቅረቡ በርካታ ሰዎች ተሰባስበውለታል። በጥሪው መሰረትም እድሜያቸው ከ7 ዓመት እስከ 85 ዓመት ያሉ በሆስፒታሉ በተመሳሳይ ቀን የተወለዱ ሰዎች በቢሻን ስታዲየም ተሰባስበው ተገኝተዋል። በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 2ሺህ 241 ሰዎች ተሰባስበው እለቱን አክብረዋል። በዚህም ክስተት የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ በተመሳሳይ ቀን የተወለዱ እና በርካታ የሰዎች ስብስብ ሲል በ2016 እትሙ አስፍሯቸዋል።

በዕለቱ በአንድ ቦታ የተገናኙት በተመሳሳይ ቀን የተወለዱ የሆስፒታሉ ደንበኞች ለረጅም ጊዜ አብረው በመቆየት እና የህይወት ልምዳቸውን እና ተሞክሯቸውን በመለዋወጥ እለቱን አብስረውታል። በተለያዩ የትውልድ ዘመን ነገር ግን በተመሳሳይ ቀን መወለዳቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትም ተበርክቶላቸዋል። ይህ አይነቱ ክስተት በ2015 በፊሊፒንስ አንድ ሆስፒታል ተደርጎ ነበር። በወቅቱ በሆስፒታሉ በተመሳሳይ ቀን መወለዳቸው የተረጋገጠው የሰዎች ቁጥር 1ሺህ 221 ነበር። 

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
419 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us