ፀባየ ሸጋ ልጅ ክፍያ እያስቀነሰ ነው

Wednesday, 22 February 2017 11:45

በጣሊያን ሚያሚ የሚገኝ አንድ ምግብ ቤት በልጆች ፀባይ ምን ያህል ቢማረር ነው እንዲህ አይነቱን ውሳኔ ሊያስተላልፍ የቻለው የሚያሰኝ ወሬ አሰምቷል። ነገሩ እንዲሁ ነው፤ አንቶኒዮ ፌራሪ የተባለው የምግብ ቤት ባለቤት ፀባየ ሸጋ ልጆች ላሏቸው የምግብ ቤቱ ተጠቃሚዎች ለተጠቀሙበት ነገር ከሚከፍሉት ክፍያ ላይ የ5 በመቶ ቅናሽ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ከባለፈው እሁድ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው ይሄ የዋጋ ቅናሽ ልጆቻቸው ጥሩ ፀባይ ኖሯቸው እንዲያድጉ ያደረጉ ወላጆችን ለማበረታታት ታስቦ የመጣ ሃሳብ እንደሆነ ባለቤቱ ተናግረዋል። የራሱ ልጆች እንደሌሉት የተገለፀው የምግብ ቤቱ ባለቤት በአሁኑ ጊዜ ወላጅ መሆን ምን ያህል ከባድ ነገር እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።

አቶ ፌራሪ ይዞት የቀረበውን ሃሳብ አንዳንዶች በመልካም ጎኑ የተቀበሉ ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ ተቃውመውታል። ሃሳቡ መልካም ነው ያሉት አካላት ልጆቻቸውን በመልካም ፀባይ ያሳደጉ ወላጆች ለስራቸው ጥሩ ምላሽ ማግኘታቸውን ደግፈውታል። በተቃራኒው ግን አንዳንዶች ምግብ ቤት ማለት ወላጆችና ልጆች በሚስማማቸው እና በለመዱት መልኩ ራሳቸውን የሚገልፁበት የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታ በመሆኑ እንዲህ አይነት መድሎ ሊደረግ አይገባም ብለዋል። አቶ ፌራሪ ግን “በምግብ ቤቴ ውስጥ ለሚሆነው ነገር ሁሉ ኃላፊነቱን የምወስደው እኔ ነኝ” ሲል ከአቋሙ ፈቀቅ እንደማይል ተናግሯል። በምግብ ቤቱ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ሁሉ የእርሱ ኃላፊነት ቢሆንም ማንኛውም አይነት ፀባይ ያለው ወላጅም ሆነ ህፃን የምግብ ቤቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ገልፆ “በተለይ ህፃናት የበለጠ እንዲመጡ እንጋብዛለን፣ ከመጡም በደስታ እንቀበላቸዋለን” ሲል ተናግሯል ያለው የዘጋርዲያን ዘገባ ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
510 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 216 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us