የዓለማችን ትንሽየዋ የምሽት ክለብ

Wednesday, 15 March 2017 12:24


ከሀገረ እንግሊዝ ሰሞኑን አንድ ዜና ይፋ ተደርጎ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ ችሏል። ነገሩ እንዲህ ነው። በሀገሪቱ ሮዘርሀም ከተማ እስከ አሁን ድረስ ከታዩ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ሁሉ ትንሽዬ የሆነችዋ ቤት መከፈቷ ነው። ይህች “ክለብ 28” የሚል መጠሪያ ያላት የምሽት ጭፈራ ቤት በሁለት ሰዎች ሃሳብ አፍላቂነት የተሰራች ቤት ናት። የምሽት ጭፈራ ቤቷ ቁመቷ 6 ጫማ ከ7 ኢንች፣ ስፋቷ ደግሞ 3 ጫማ እንዲሁም ከመሬት ወለል በታች ያላት ጥልቀት 5 ጫማ ነው። ይህች የምሽት ጭፈራ ቤት ዘመናዊ እና ጥራቱን የጠበቀ የድምፅ መሣሪያ የተገጠመላት፣ ምቹ የሆነ የዳንስ መድረክ ያላት እንዲሁም በሯ ወደ ውጭ የሚከፈት ዘናጭ የጭፈራ ቤት ናት። ለመሆኑ ይህች ቤት ምን ያህል ሰዎችን የማስተናገድ አቅም አላት? ብለው የሚጠይቁ ካሉ ቤቷ 6 ሰዎችን እና አንድ ሙዚቃ አጫዋች (ዲጄን) አንደላቃ ማስተናገድ ትችላለች።

የዚችን የትንሽዬ የምሽት ጭፈራ ቤት ሃሳብ ያመነጩት ጄራርድ ጀርኪንስ ኦማር እና ስቴፈን ሮብሰን እንደገለፁትም ቤቷን የመገንባት ሃሳቡ የመጣላቸው በከተማዋ ለየት ያለ እና አዝናኝ የሆነ ነገር ለመፍጠር በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል። ከተማዋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በበርካት ምቹ ያልሆኑ ነገሮች ውስጥ ማለቷን የገለፁት የሃሳቡ አፍላቂዎች፤ እነርሱም የአቅማቸውን በመስራት ለአካባቢው ህዝብ ዘና የሚያደርግ ነገርን ለመፍጠር አስበው እንዳደረጉት ተናግረዋል። እግረ መንገዳቸውንም የምሽት ጭፈራ ቤቷ በዓለማችን ትንሿ በመሆኗ በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ እንድትሰፍርላቸው ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። ይህን ሂደት ለመከታተል ያግዛቸው ዘንድም ወደ ምሽት ቤቷ የሚመጡ ሰዎች መጠነኛ ክፍያ እንዲከፍሉ የማድረግ ሃሳብ አላቸው ሲል ያስነበበው ዩናይትድ ፕሬስ ኢንተርናሽናል ነው። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
372 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 212 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us