ማንነትን መቀየር ይቻላል?

Wednesday, 15 March 2017 12:23

 

በድሮ ጊዜ ግሪካውያን ብዙ አማልክት ነበሯቸው። እነዚህም አማልክት በየጊዜው እየተገናኙ ስለሰውም ሆነ ስለተቀሩት ፍጥረታት ጉዳይ ይወያዩ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን የቀረበው የውይይት አጀንዳም “የሰውንም ሆነ የሌሎች እንስሳት ባህርይ መቀየር ይቻላል?” የሚል ነበር። በዚህም መሠረት ጁፒተር የተባለው አምላክ “ለምን አይቻልም፤ ይቻላል እንጂ” ሲል ቬኑስ የተባለችው አምላክ “በፍጹም የሚቻል አይደለም” ስትል ተከራከረች። በዚህም መሠረት ጥያቄውን በተግባር ለመተርጎም ይቻል ዘንድ ጁፒተር አንዷን ድመት ወደ ውብ ሴትነት ቀየራት። እናም ለአንድ ወጣት ዳረለት። ሠርጉም በጣም ያማረ ስለነበር ጁፒትር በሥራው ተደነቀ። የኩራት መንፈስ እየተሰማው ወደ ቬኑስ ዘወር አለናም “አየሽ አይቻልም ስትይ እንደተቻለ፣ ሙሽራይቱንስ እንዴት እንደቻለችበት አስተዋልሽ? አሁን ይችን ማን ድመት የነበረች ናት ብሎ ያምናል?” በማለት በአድናቆት ጠየቃት።

የተፈጥሮ ባህርይ አይለወጥም በማለት የተከራከረችው ቬኑስም ትክክል መሆኗን ለማሳየት አሥራ የያዘቻትን አይጥ ሙሽራይቱ ወዳለችበት አቅጣጫ ለቀቀቻት። እንደለቀቀቻትም የአሁኗ ሙሽራ የቀድሞዋ ድመትም አይጧን እንዳየች ከተቀመጠችበት ብድግ አለችና አይጧን ማሳደድ ጀመረች።

በዚህ ጊዜ ቬኑስ “አልነገርኩህም የተፈጥሮ ባህርይ ሊቀየር አይችልም” አለችና ነገረችው።  

                              የኤዞፕ ተረቶች - በተሾመ ብርሃኑ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
344 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 215 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us