የዘራፊው የድረሱልኝ ጥሪ

Wednesday, 22 March 2017 12:10

 

ከወደ አሌክሳንድሪያ ሰሞኑን አንድ ወሬ ተሰምቶ አለምን አስደንቋል። አሶሲየትድ ፕሬስ ከአሌክሳንደሪያ እንደዘገበው ቤት ዘራፊው እግሬን ተሰበርኩ ብሎ ባቀረበው የድረሱልኝ ጥያቄ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የ21 አመቱ ወጣት ልዑል ዮሴፍ በቨርጂኒያ ወደሚገኝ አንድ መኖሪያ አፓርታማ ያመራል። አፓርታማው ውስጥ ገብቶ ዝርፍያ በመፈፀም ላይ ሳለም ባለቤቱ ወደ ቤቱ መመለሱን ይረዳል። ይሄን ጊዜም መውጫ ያጣው ዘራፊ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ካለው አፓርታማ በመስኮት በኩል በመዝለል ለማምለጥ ሙከራ ያደርጋል። ነገር ግን መሬት ላይ ሲያርፍ በእግሩ ላይ ጉዳት ስላጋጠመው ድረሱልኝ ሲል በ911 የጥሪ መልዕክት ያስተላልፋል። ፖሊስም ተከታትሎ ለሰራኸው ስራ ትቀጣለህ ሲል በቁጥጥር ስር አውሎታል።

መኪናውን አቁሞ ቤቱን ለመዝረፍ ወደ አፓርታማው የወጣው ዮሴፍ፤ ፖሊስም የመኪናውን ዱካ ተከትሎ በቁጥጥር ስር እንዲውል አድርጎታል። እግሬን ስለተሰበርኩ ድረሱልኝ ተብሎ የስልክ ጥሪ የደረሰው ፖሊስም ወደ ስፍራው በማምራት የዝርፊያ ሙከራ ተደርጓል በተባው አባርታማ አጠገብ ዮሰፍን አግኝቶታል። በመሆኑም ክስተቶቹን አገጣጥሞ በመመልከት ዮሴፍን ወደ ሆስፒታል የላከው ሲሆን፤ ህክምናውን አጠናቆ ከሆስፒታል እንደወጣም ክስ ይመሰረትበታል ተብሏል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
356 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us