ስለ አውቶሞቢል ነጂዎች

Wednesday, 29 March 2017 12:07

 

ማናቸውም አቶሞቢል ሲያልፍ ማንም ሰው ወይም ልጆች በደንጊያ ወይም በሌላ ነገር ኦቶሞቢል ወይም ጋሪ ሲመቱ የተገኙ እንደሆነ ኮሚሳሪያ የቆረጠውን መቀጫ ይከፍላል። የኦቶሞቢሉም መሳርያ ቢበላሽ ዋጋውን በእጥፍ ይከፍላሉ። ደግሞ ኦቶሞቢል ነጂዎች እሚሄዱበት ቦታ ሲደርሱ ወይም ወደሚገቡበት ቤት የሚወስድ መንገድ በሚያቋርጥበት ሥፍራ ለመድረስና ኦቶሞቢላቸውን ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራቸው ለማዞር ሲቀርቡ አስቀድመው እጃቸውን ዘርግተው የሚዞሩበትን ወገን ለሕዝቡ ማሳየት አለባቸው። በሚያዞሩበትም ጊዜ ማሰሚያቸውን ደጋግመው መንፋት ይገባቸዋል።

በከተማ መንገድ ላይ ሕዝብ የሚዛወርበትንና የሚመላለስበትን ደንብ ለማስታወቅና ለማስጠንቀቅ ሲል መንግስት ከዚህ በላይ የተፃፈውን ልዩ ልዩ መቀጫ በህዝቡ ላይ መወሰኑ ኦቶሞቢል ነጂዎች ደንባቸውን እንዳይተላለፉ አይደለምና በብርቱ ተጠንቅቀው ኦቶሞቢላቸውን መንዳት አለባቸው። ሕዝቡም ይልቁንም ከአገር ቤት የሚመጣው እንግዳ ደራሽ የኦቶሞቢል ነገር ምን እንደሆነ የማያውቅ ነውና ብዙ ሕዝብ በሚሄድበት መንገድ ሲያልፉ ነጂዎቹ ማሰሚያቸውን ያለማቋረጥ መንፋት አለባቸው፡፤ ሲነፉም እንኳን እንግዳው የማሰሚያው ድምጥ ምንማለት እንደሆነ የሚያውቀው ስላልሆነ ኦቶሞቢል ነጂዎች በዝግታ መሄድ አለባቸው። ይህንን ሥርዓት ተላልፈው ኦቶሞቢላቸው ሰው የዳጠ እንደሆነ ካሳ ወይም የነፍስ ዋጋ መክፈላቸው አይቀርም። ደግሞ በከተማ ውስጥ የሚሄድ ኦቶሞቢል እጅግ ቢበዛ ከአምሳ ኪሎ ሜትር የበለጠ እንዳይሄድ ተከልክሏል።

ኦቶሞቢል ነጂዎቹ ሲነዱ የፊታቸውን ኦቶሞቢል ለመቅደም ሲፈልጉ በቀኝም ቢሆን በግራ በፈቀዳቸው በኩል አስቀድመው ያልፋሉ። ይኸውም ብርቱ አደጋ የሚያመጣ ነውና ለመቅደም የፈለገ ባለኦቶሞቢል አስቀድመኝ ብሎ ማሰሚያውን መላልሶ ነፍቶ እፊቱ ያለው የግራውን ወገን ሲለቅለት እርሱም ወደ ግራው ፈቀቅ ብሎ ይለፍ እንጂ በማናቸውም በፈቀደው ወገን ማስቀደም በጭራሽ ተከልክሏል። ኦቶሞቢል ነጂ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ይህንን ደንብ ሲተላለፉ የተገኙ እንደሆነ ኮሚሳርያ ዳኞች የቆረጡትን መቀጫ ይከፍላሉ።

ደግሞ ብዙ ሰዎች ኦቶሞቢላቸውን ወይም ካሚዮናቸውን በመንገድ መካከል እያቆሙ መንገደኛው እንዳይተላለፍ ያሰናክላሉ። ከዛሬ ጀምሮ ግን ባለ ኦቶሞቢልና ባለ ካሚዮን የተባለ ሁሉ ኦቶሞቢሉን ወይም ካሚዮኑን በማናቸውም ምክንያት ማቆም ያስፈለገው እንደሆነ መንገዱ ወደ ግራ ለቅቆ ወደ ቀኙ ጠረፍ ያቁም። ይህን ደንብ ተላልፎ ማናቸውንም ጋሪ ሁሉ በመካከል መንገድ ወይም ከመንገዱ በስተግራ አቁሞ የተገኘ ባለሰረገላ ሁሉ የኮሚሳርያ ዳኛ የቀረጠውን መቀጫ ይከፍላል። ደግሞ ማናቸውንም ነገር እንደ ድንጋይ ፣ እንጨት፣ እቃም ቢሆን በመንገድ ላይ ጥሎ መንገደኛው እንዳይተላለፍ የሚያሰናክል ሰው ሁሉ ይህንኑ መቀጫ ይከፍላል።

                ከቤተ መንግስት ዶሴ - የብላታ ወልደማርያም መዘክር

                                     በመኩሪያ መካሻ

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
296 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 215 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us