በጃፓን የመንጃ ፍቃድ ለመለሰ የቀብር ዋጋ ይቀንሳል

Wednesday, 29 March 2017 12:10

 

ሀገረ ጃፓን እድሜያቸው የገፉ ሰዎች መኪና እያሽከረከሩ ስላስቸገሯት አንድ አዲስ ነገር ይዛ መጥታለች። የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለፁት የእድሜ ባለፀጋዎች የመንጃ ፈቃዳቸውን በፈቃዳቸው የሚመልሱ ከሆነ የቀብር አገልግሎት ክፍያ ላይ ቅናሽ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል። የሀገሪቱ የመንገድ ባለስልጣኖች ከአንድ የቀብር አስፈፃሚ ድርጅት ጋር በደረሱት ስምምነት እድሜያቸው በመግፋቱ የመንጃ ፈቃዳቸውን ለመመለስ ፍቃደኛ ለሆኑ ሰዎች የቀብር ወጪያቸውን የ15 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ያደርጋል። ኪዮንዶ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው የዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን የፈለገ የሀገሪቱ የእድሜ ባለፀጋ ወደ አካባቢው ፖሊስ ጣቢያ በማምራት የመንጃ ፈቃዱን ማስረከብ ብቻ በቂ ነው። በዚህ ተግባር ላይ የሚሳተፉ ሰዎች የሚደረግላቸው የቀብር አገልግሎት ዋጋ ቅናሽም ለሌሎች የቤተሰብ አባላት ጭምር እንደሚተርፍም ተገልጿል።

በጃፓን እድሜያቸው በጣም የገፉ ሰዎች መኪና የማሽከርከር ልምድ ያላቸው ሲሆን፤ ከእርጅናቸው የተነሳ የነዳጅ መስጫ እና ፍጥነት መቆጣጠሪያውን መለየት እያቃታቸው በርካታ አሰቃቂ አደጋዎች እየተከሰቱ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። በ2015 ብቻ በሀገሪቱ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን የሚሆኑ እድሜያቸው ከ75 ዓመት በላይ የሆኑ የእድሜ ባለፀጎች መኪና እያሽከረከሩ እንደነበረ ዘ ጃፓን ታይምስ ዘግቧል። ይህ ቁጥር ከአለፉት አስርት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በእጥፍ የጨመረ ሲሆን፤ በዚህ ሳቢያ የሚደርሰው የመኪናዎች ግጭትም የዚያኑ ያህል መጨመሩን ዘገባው አመልክቷል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
352 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 214 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us