ጭጋግ ዘመኖች

Wednesday, 05 April 2017 12:21

 

ከተስፋው ሰማይ ላይ ከዋክብት፣ ፀሐዩን አውርዶ እየጣለ

ከማንነት ማማው፤ ከክብሩ ሰገነት በመሰልጠን ስካር ቁልቁል የዘለለ

ዛሬውን የሚያስረጅ እድሜውን ቀርጣፊ እንደኛ ማን አለ?

በነገው ማሰሮ የኮመጠተ ወይን፣

                  እጅ እጅ የሚል አሹቅ አስሮ የሚያሳድር

አዳዲስ ቀናትን በአሮጌ ዕለታት አራፊ እየጣፈ

                  ከውበት ጥለት ላይ ማስቀየም የሚያኖር፤

ደጁን ካሳመረው ዘርፋፋ ወይራ ላይ ማዶ ያሉ ሰዎች ሞፈር እንዲያበጁ

                                                አዋጅ ያስነገረ

አንደኛ ማን አለ ከብርሃን ተሰርቶ፣ ባለፉት ዘመናት በጭጋግ የኖረ?

የጣልናትን ፀሐይ አፋፍሰው ያኖሯት ቅንጥብጣቢ ብርሃን ሲቸረችሩልን

እንደ መሰልጠን ጥግ፣ እንደ ክብር አይተነው ተሻምቶ መግዛቱን፣

እንደኛ ማን አለ ደረት አሳብጦ እውርደት መንበር ላይ ላመታት የባጀ

የመታደስ ጽንሱን በመርዝ አጨንግፎ፣

            በብል አስተሳሰብ መፃኢ አጣውን ርዕዩን ያጃጀ?

      (ትልቅ ነበርን፤. . . . . እንደማለት)

*** *****  *****

እንቆቅላችሁ.  . .  .. .

የሚያፏጭ ጉብል በተበሳሰከ አንቀልባ ታቅፋ፤

      የነበርን ዜማ እያንጎራጎረች ነጭናጫ ሙጫዋን እሹሩሩ ምትል፤

የመሆን ሁዳዷን ያለመሆን ክርዳድ ዘርታ ምታጠፋ፤

                  መሆንን ለማጨድ አለቅጥ ምትባትል?

. . . .. ሐገር ስጡኝ፤

      . . . .  እዚህ ኼጄ ምን አጥቼ!!!

            ትናንት አናት፤

                  ዛሬ ጅራት፣

            ነገ ደግሞ በማለዳ ተነስቼ

                  የቁም ተዝካር ደግሳለሁ እንዳትቀሩ ዘመዶቼ።

(ትልቅም < ትል (ል) ቅም. . . .

                     ጭጋግ ዘመኖች - በዮናስ ውበሽት

ይምረጡ
(2 ሰዎች መርጠዋል)
347 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 217 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us