ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋዮቹ የአፍሪካ መሪዎች

Wednesday, 05 April 2017 12:23

 

ብዙዎች የስልጣን ወንበርን መቆናጠጥ ከሚፈልጉባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በስልጣን ዘመናቸው እና ከዚያ በኋላ የሚያገኙት ጠቀም ያለ ገንዘብ ነው። አንዳንድ ፖለቲከኞች ደግሞ የስልጣን ዘመን ክፍያ ይቅርብን ብለው በዓለም ላይ ታሪክ አስመዝግበው ሲያልፉ ታይተዋል። ከእነዚህ ሰዎች መካከልም በቅርቡ ስልጣን የያዙት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተጠቃሽ ናቸው። ከዚህ ወጣ ባለ መልኩ በሀጉረ አፍሪካ በየዓመቱ ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፈላቸውን መሪዎች ዝርዝር ቢዝነስ ኢንሳይደር እንዲህ አቅርቦታል።

11ኛ. አብድል ፋታህ አል ሲሊ፤ የግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ከከፍተኛ ደሞዝተኞች ተርታ በ11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሲሆን ዓመታዊ ደሞዛቸውም 70ሺህ 400 ዶላር ነው።

10ኛ. ጆን ድራሚን ማሐማ፤ ማሓማ የጋና ፕሬዝዳንት ናቸው። ፕሬዝዳንቱ የስራ አበላቸውን እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞቻቸውን ሳይጨምር በዓመት 76ሺህ ዶላር ይከፈላቸዋል።

9ኛ. ፓውል ካጋሜ፤ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፓውል ካጋሜ ዘጠነኛው ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይ አፍሪካዊ መሪ ናቸው። ይሄ ብቻም ሳይሆን ካጋሜ በምስራቅ አፍሪካ ሁለተኛው ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይ መሪ ናቸው። የእኚህ ፕሬዝዳንት ዓመታዊ ደሞዝም 85ሺህ ዶላር ነው።

8ኛ. ኤለን ጆንሰን ሰርለፍ፤ የላይቤሪያዋ ፕሬዝዳንት ሰርሊፍም የዋዛ ሰው አይደሉም። በብዙ ነገር ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው የሚታወቁት ሰርሊፍ በዓመት የ90ሺህ ዶላር ደሞዝተኛ ናቸው።

7ኛ. አላሳኔ ኦታራ፤ የአይቨሪ ኮስት ፕሬዝዳንት የሆኑት ኦታራ በዓመት የሚያገኙት ደሞዝ 100ሺህ ዶላር ነው።

6ኛ. ሒፊኬፕዌ ፕሐምባ፤ እኚህ ሰው የናሚቢያ ፕሬዝዳንት ሲሆኑ ዓመታዊ ደሞዛቸውም 110 ሺህ ዶላር ነው።

5ኛ. ዴኒስ ሳሶ ንጉሶ፤ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት የሆኑት ንጉስ በዓመት የሚከፈላቸው ደሞዝ 110ሺህ ዶላር ነው።

4ኛ. ኢኮሊሎ ድሆኒኒ፤ ድሆኒኒ የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት ናቸው። እኚህ ሰው በዓመት 115ሺህ ዶላር እንደዋዛ ቆጥረው የሚረከቡ ባለስልጣን ናቸው። 

3ኛ. ኡሁራ ኬንያታ፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ኬንያታ ከምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ከፍተኛ ደሞዝ ተከፋይ መሪ ናቸው። ከአፍሪካ መሪዎችም በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እኚሁ ሰው አበላቸውን ሳይጨምር በዓመት 132ሺህ ዶላር ተከፋይ ናቸው።

2ኛ. አብደላዚዝ ቡቶፍሊካ፤ የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት ቡቶፍሊካ ዓመታዊ ደሞዛቸው 168ሺህ ዶላር ነው።

1ኛ. ጃኮብ ዙማ፤ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዙማ ከአፍሪካ መሪዎች ሁሉ ከፍተኛው ደሞዝተኛ ናቸው። እኚህ ሰው በየዓመቱ 272 ሺህ ዶላር ይከፈላቸዋል። 

ይምረጡ
(5 ሰዎች መርጠዋል)
624 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 213 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us