ስለ ዘበኞች

Wednesday, 12 April 2017 12:05

 

ይህ ከዚህ በላይ የተፃፈ ሥርዓት ሁሉ በትክክል ሆኖ እንዲፈፀም የመንግሥት ዘበኞች የመለዮ ልብሳቸውን ለብሰው የሚጠብቁ ስለሆኑ ሕዝቡም ከታላላቆች መኳንንት ዠምሮ እስከ ተርታው ሰው የዘበኛን ቃል መስማትና መታዘዝ አለበት። ነገር ግን ይህንን ስለተባለ መንግሥት የሚያቆመውን ሕግና ደንብ ለህዝቡ እያመለከተ ሕጉንና ደንቡን ለማስፈፀምና ለማጠናከር ነው እንጂ ዘበኞች እንደፈቃዳቸው ሕዝቡን ለማጉላላትና ለማጥቃት እንዲቻላቸው አይደለም። ስለዚህ ዘበኞች በታዘዙበት ቦታ ሆነው በየመንገዱ እየተመላለሱ ከሕጉና ከደንቡ የወጣና ያለአገባብ የሆነ ነገር እንዳይደረግ ተጠንቅቀው መጠበቅ አለባቸው።

ሕዝቡም የተደነገገለትን ደንብና ህግ ጠብቆ እንዲተላለፍ በትህትና ቃል እያመለከቱ ማስተላለፍ የዘበኞች ሥራ ነው። መንገድና ቤትም የተሳሳተውን መንገድ ማሳየት አለባቸው። መንገደኛም የሚጠይቃቸውን መንገድ ለማሳየት እንዲቻላቸው ዘበኞች አስቀድሞ የከተማውን መንገድ በየክፍላቸው ማወቅ አለባቸው። ዋናውም ስራቸው ሁለት መንገድ በሚያቋርጡበት መካከል እየቆሙ መንገደኛው እንዳይጋጭ በየተራው ማስተላለፍና ወዲያና ወዲህ እየተንጎራደዱ መጠበቅና ከደንብ የወጣውን መንገደኛ እንደ ደንቡ ማስሄድ ነው። ከዚህም ሌላ ደግሞ አምባጓሮ በተነሳበት ሥፍራ በአዕምሮ ቃል እየተናገሩ ጠበኛውን ወደ ኮሚሳርያው መውሰድ አለባቸው። ወደ ዳኛው ለመሄድ የሚያስቸግርና ወደ ዳኛ አልሄድም የሚል ሃይለኛ ሰው ቢያገኛቸው ሶስትና አራት ሆነው መያዝና ወደ ዳኛ መውሰድ ነው እንጂ ገላመጠን ወይም ሰደበን ብለው ማናቸውንም ሰው መምታት፣ ማጉላላት አይገባቸውም። በዘበኝነታቸውም እያመካኙ ሰውን ሲያጉላሉና ሲያውኩ ቢገኙ ግን በብርቱ ቅጣት ይቀጣሉ። ደግሞም ከዚህ በላይ በየክፍሉ የተፃፈውን የተከለከለ ነገር ሁሉ ሕዝቡ እየተላለፈ ለራሱ የሚጎዳበትን ነገር እንዳያደርግ ዘበኞች ተጠንቅቀው መጠበቅና ሕዝቡን ማስጠንቀቅ ግዴታ አለባቸው። ዘበኞች ግን በደንብ የታዘዙትን ሥራ ሰበብ እያደረጉ ሕዝቡን ሲያጉላሉና ያልታዘዙትን ስራ ሲሰሩ የተገኙ እንደሆነ ሕግ አስተማሪና ጠባቂ መሆናቸው ቀርቶ ሕግ አፍራሾች መሆናቸው ነውና ተርታ ከሚቀጣበት ቅጣት በጣም በበለጠ ቅጣት ሊቀጡ ይገባቸዋል።

ይህ የአዋጅ ረቂቅ ለአገር ግዛት ሚኒስትርና ለጃንሆይ ተሰጥቷል።

ጥቅምት 1922

                        ከቤተ መንግስት ዶሴ - የብላታ ወልደማርያም መዘክር

                                    በመኩሪያ መካሻ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
419 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 211 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us