ጂ.ኤስ. ዲ

Wednesday, 12 April 2017 12:07

 

ጃንሆይ ከ3 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ድረስ በአዳራሹ ኃላፊነቶችን ሲያደላድሉ ይቆያሉ። ስለዚህ ይህ ሰዓት የኃላፊነት ማደላደያ ሰዓት ይባላል።

መኳንቱና ለሹመት የታጩ ሰዎች ለጥ ብለው እጅ እየነሱ ንጉሱ ወደ አዳራሹ ይገባሉ። ከዛ በዙፋናቸው ላይ ይቀመጣሉ። ልክ ሲቀመጡ እኔ እግራቸው ስር ትራስ አስገባለሁ። ይህም ልክ እንደ መብረቅ ብልጭታ ባለ ፍነት መከናወን አለበት። ምክንያቱም የንጉስ ነገስታችን እግር ለሰኮንድ ሽራፊ እንኳ በአየር ላይ መንጠልጠል ስለሌለበት ነው። ሁላችንም ጃንሆይ አጭርና ትንሽ ፍጡር እንደሆኑ እናውቃለን። በዛው መጠን የንጉሰ ነገስቱ ክብር ጠባቂ ቢሮ ንጉሱ በማንኛውም መልኩ  በአካልም ቢሆን ከአሽከሮቻቸው ከፍ ብለው መታየት እንዳለባቸው እናምናለን። ስለዚህ የንጉሰ ነገስት ዙፋች ረጃጅም እግሮችና ከፍ ያሉ መቀመጫዎች ነበሯቸው። በተለይ በጣም ግዙፍ የነበሩት የአፄ ምኒልክ ዙፋኖች።

ስለዚህ በጃንሆይ ቁመትና በዙፋኖቹ ትልቅነት መሃል ተቃርኖ ተፈጠረ። በተለይ በእግራቸው አካባቢ ልክ እንደ ህጻን ልጅ እግሮች በአየር ላይ ተንጠልጥለው የሚንፈራገጡ ሰው ተገቢውን ክብርና መፈራት ያገኛሉ ብሉ መገመት ያስቸግራል። ስለዚህ ትራሶቹ ይህንን ክፍተት በመሸፈን ሊከሰቱ የሚችሉ እንቆቅልሾችን በሙሉ አስቀርተዋል።

እኔ ለ26 ዓመታት የግርማዊ ጃንሆይ ትራስ ያዥ ነበርኩ። ጃንሆይን በአለም ዙሪያ አጅቤያቸው ዞሬያለሁ። እውነቱን ልንገርህ ያ ለኔ ታላቅ ክብር ነበር።

ግርማዊነታቸው ያለኔ የትም አይንቀሳቀሱም። ጃንሆይ በሄዱበት ሁሉ ለክብራቸው በዙፋን ላይ መቀመጥ አለባቸው። በዙፋን ላይ ደግሞ ያለ ትራስ አይቀመጡም። እኔ ደግሞ የሳቸው ትራስ ያዥ ነበርኩ። ይህን ልዩ ሙያ ተክኜዋለሁ። እንዲያውም የልክፍት ያህል ነበር። በየትኛውም አለም ስላለው የዙፋን ከፍታ እውቀት ነበረኝ።

ስለዚህም በሰከንድ ውስጥ ተስማሚውን ትራስ መምረጥ እችል ነበር። ስለሆነም በንጉሱ እግርና በትራሱ መሃል የአንዲት ሴንቲ ሜትር ክፍተት ኖሮ አያውቅም። በመጋዘኔ ውስጥ ሃምሳ ሁለት ከተለያዩ ጨርቃ ጨርቆች የተሰሩ የተለያዩ መጠንና ቀለም ያላቸው ትራሶች ነበሩ።

እኔ ራሱ ያለማቋረጥ አቀማመጣቸውን እከታተል ነበር። ዝንቦች እዚያ ላይ እንቁላላቸውን አይጥሉም። ይህ አይነቱ ክስተት ተከስቶ ቢታይ እጅግ አሳፋሪ ውርደት ያስከትላል።  

                  ምስጢራዊው ንጉስ ቀ.ኀ.ስ - በዮሐናን ካሣ

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
441 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 970 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us