የፍቅር ሳቅ

Wednesday, 26 April 2017 12:13

በሰሙት ባ’ዩት፣

ባስተዋሉት፣

ተደስተው ሲስቁ፣

እያሽካኩ ሲሳለቁ፣

ቢንካኩ ቢሽኮረመሙ፣

በፍላጣው በልማሙ፣

ባንፀባራቂው በመልካሙ፣

ውብ ጥርሳቸው እያዜሙ፣

ክርክር ብለው ተንካትክተው፣

ያድማጭን ቀልብ ስበው፣

ሲስቁ ባይ ተመስጨ፣

በሃሳብ ተናውጨ፣

ዕኔም ሳቅኩኝ ወጉ ደርሶኝ፣

ፍቅር ልቤን አምከንስኖኝ፡፡

ከኔ ርቃ ሩቅ ሁና፣

ፍቅሯን በልቤ ትታ፣

አደራዋን አበርትታ፣

እሷነቷን ለኔስ’ታ፣

መላ አካሌን አመናታ፣

አሳቀችኝ የልብ ሳቅ፣

ሰው ያላየው የፍቅር ሳቅ

ለኔው ለራሴ በድብቅ፡፡

            (የፍቅር ሳቅ፤ የግጥም መድብል የተወሰደ ከገጣሚ ደሳለኝ ማስሬ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
260 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 724 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us