የአስመራና የድሬዳዋ ቡድኖች

Wednesday, 26 April 2017 12:15

 

የኛ ጫማ ሰፊዎች የፈረንጁን ሞዴል እያዩ የሚሰሩ ቀልጣፎች መሆናቸው ተመስክሮላቸዋል፡፡ ለመለካትም ሆነ ፕሮቫ ለማድረግ የሚሄደውን ቡና ወይም ሻይ መጋበዝ ተለምዷል፡፡ የብስክሌት ተወዳዳሪ የነበረው አቶ አበበ ማሞ ጥሩ ጫማ ሰፊ ነበር፡፡ የአሥመራና የድሬዳዋ ቡድኖች በኢትዮጵያ ሻምፒዮና መካፈል በመጀመራቸው የፉትቦል ጨዋታ ተስፋፋ፡፡ ከጥንት ጀምሮ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብዙ ቀልጣፋ ተጫዋቾች ስለነበራቸው፤ ለልዩ ልዩ ክለቦች ይጫወታሉ፡፡ በዚያን ጊዜ በእነ ጌታቸው መድሃኔ፣ መስፍን ወልደማርያም፣ ኃይሉ አፈወርቅ፣ ልዑል ሰገድ በቀለ፣ ንጉሤ ፍትአወቅ፣ እልፍ አግድ ጎበና፣ ፀጋዬ በቀለ፣ ዘውዴ ሳሙኤልና ሌሎችም የነበሩበት የተፈሪ መኮንን ት/ቤት ቡድን የጦር ሰራዊትን ቡድን አሸንፏል፡፡ ወዳጁ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በተከላካይ ስፍራ ይጫወት ስለነበር አሁንም የመከላከል ተግባሩን ቀጥሏል፡፡ ምንም አርቢትሩ ቀይ ካርድ እያሳየ ቃሊቲ ቢከተውም፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖለቲካ ቡድን መጫወቱን አላቋረጠም፡፡ የሳንጆርጅ ተጫዋች የነበሩት ልዑልሰገድ፣ ዘውዴና ፀጋዬ ለብሔራዊ ቡድንም ተጫውተዋል፡፡

ቀልጣፋው አላ (ክንፍ) ተጫዋችና አብዶ በመሥራት የታወቀው ነፀረ ወልደሥላሴ ከዳግማዊ ምኒልክ ት/ቤት ሲሆን፣ ግብ ጠባቂው ደግሞ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ ከኮተቤ ት/ቤት ነው፡፡ ሁለቱም ለብዙ ዓመታት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውተዋል፡፡ በጦር ሠራዊት፣ ክብር ዘበኛ፣ አየር ኃይልና ፖሊስ ቡድኖች ውስጥ ይጫወቱ የነበሩት አብዛኞቹ ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተመልምለው በአካዳሚዎች የሚማሩ ዕጩዎች ወይም የተመረቁ መኮንኖች ናቸው፡፡ ከብዙዎቹ መካከል የማስታወሳቸው ዘገየ እምሩ፣ ረጋሳ ጂማ (ክብር ዘበኛ)፣ ሚካኤል ክብሩ፣ ሠናይ ሀብተገብርኤል፣ ጌታቸው ከንፈሬ፣ አበበ አባተ፣ ፋንታ በላይ፣ ግዛው ትዕዛዙ፣ ሸዋፈራሁ አስፋው፣ ጌታቸው ነጋሽ (አየር ኃይል) ዋሲሁን ጋሻው (ጦር ሠራዊት) ናቸው፡፡

በ1959 ነው ዝነኞቹ መንግሥቱ ወርቁ፣ አዋድ መሐመድ፣ ከነሉቺያኖና ኢታሎ ቫሳሎ ጋር ለብሔራዊ ቡድን መሰለፍ የጀመሩት፡፡ የአዲስ አበባ ት/ቤቶች በእግር ኳስ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የስፖርት ዓይነቶች ይታወቃሉ፡፡ ያኔ የነበሩት ሰውነታቸውና ቁመታቸው ለአትሌቲክስ የተስተካከለ በመሆኑ፣ ባሁኑ ጊዜ ቢገኙ ኖሮ ውጤታቻው በአጭር ርቀት ያማረ እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡ ኮቴቤ የነበሩት ሁለቱ ወንድማማቾች ተፈሪና ክፍሌ በላይ የ200 ሜትር አሯሯጥ ድቅን ይልብኛል፡፡ እንዲሁም በ100 ሜትር የአበራ ካሳና የንጉሤ ሮባ በ400 ሜትር አደም አብደላ (ከተፈሪ መኮንን ት/ቤት) የሁሴን ሮብሌና ሰይድ ሙሳ (ከመድሃኔዓለም)፣ በከፍታ ዝላይ የሽፈራው አጉናፍር (ከጄኔራል ዊንጌት) ብቃት አይረሳም፡፡ ለሳንጆርጅ እየተጫወቱ ሩጫንም የሚያዘወትሩት ዳምጤ ኃይሌ፣ ዑመር ሮያሌና ነፀረ ወልደሥላሴ ቀልጣፋ አትሌቶች ናቸው፡፡

                              (የፒያሳ ልጅ ፍቅሩ ኪዳኔ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
254 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 465 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us