የአንድ ኢትዮጵያዊ ቴሌቪዥን አጭር የሕይወት ታሪክ

Wednesday, 03 May 2017 12:19

 

ቴሌቪዥኑ

ሰውዬውን ዐየው

ሰውዬው ያፈጣል

ሻጋታ መረጃ ባ’ይኑ ያላምጣል።

ዐይኑን ላፍታ ማርገብ ከሽንፈት ቆጥሮ

ያይኖቹን ሽፋሽፍት በችካል ወጥሮ

ባዶና ት’ይንቱን በቅጡ ሳይለዬው

ያፈጣል፣ ያፈጣል፣ ያፈጣል ሰውዬው።

እግዜሀር ደግ ነው

ዐይንን ባ’ምፖል አምሳል ግንባር ላይ ቢተክልም

ሲያበሩበት ቢያድሩ ላይን አያስከፍልም።

ግን ቴሌቪዥኑ

ታካች የፈጠረው ታካች በመኾኑ

ለውጥ እየተመኘ

ክፍሉን ባ’ይኑ ቃኘ

ካፍጣጩ ሰው በቀር ምንም አላገኜ

ስለዚህ ሰለቸው፣ ታከተው ተከፋ

እኩለ ሌሊት ላይ ራሱን አጠፋ።

                              ስብስብ ግጥሞች /በዕውቀቱ ስዩም/

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
217 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 919 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us