በውበት አላምንም

Wednesday, 17 May 2017 12:28

 

በቀን መመላለስ የታከታት ፀሐይ

በሌት እስከትወጣ

በጥቢ መቀጠር የሰለቻት አደይ

በበጋ እስክትመጣ

በውበት አላምንም

ባለቅኔ አልኾንም

ዋርካ ሽቅብ ሄዶ

የርግብ ክንፍ በመውረስ

’ርግብ ሥርን ሰዶ

እስኪተከል ድረስ

በውበት አላምንም

ባለቅኔ አልኾንም።

ሠዓሊዎች ሁሉ

የቀለም ዘር ሁላ ከንቱ ነው እያሉ

ባ’የር ብራና ላይ በጭስ እስኪስሉ

በውበት አላምንም

ባለቅኔ አልኾንም።  

            (ስብስብ ግጥሞች - ከበዕወቀቱ ስዩም)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
217 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us