ተጫዋች ሰው

Wednesday, 14 June 2017 12:35

 

አንድ ተጫዋች ሰው ከዕለታት አንድ ቀን በመንገድ ሲያልፍ ነገር በሆዱ ገብቶ ያሰላስል ኖሮ አንድ ሌላ ተላላፊ መንገደኛ ሰው አይቶ ጤና ይስጥልኝ አለና ሰላምታ ሰጠው። ግን ወዲያው ልብ ብሎ ቢመለከተው በመልክ እንደ ተሳሳተ ተረዳውና ቀረብ ብሎ ወንድሜ ሆይ ይቅርታህን አድርግልኝ ሰላምታ የሰጠሁህ አንድ የማውቀው ሰው አለ በገጥታህ እሱን መስለኸኝ ነው አለው። ያ መንገደኛ ደግሞ በበኩሉ ኧረ ታልህስ እኔም እንደዚሁ መጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁህ አንድ ወዳጄ የሆነ ሰው አለ እሱን መስለኸኝ ሰላምታ ልሰጥህ ቃጥቶኝ ነበረ አለው። ተጫዋቹ ሰው ይኸን በሰማ ጊዜ ፊቱን በደስታ አብርቶ እየሳቀ የተሳሳትነው ለካ ሁለታችንም ነንና እንግዲያውስ በል ተወው እኔም እኔ አይደለሁ አንተም አንተ አይደለህ ብሎት መንገዱን ቀጠለ።

                        (“ታሪክና ምሳሌ”- ከከበደ ሚካኤል) 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
319 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1063 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us