የጃንሆይ የገንዘብ አሰጣጥ “ደብሊው. ኤ. ኤን” እንደፃፈው

Wednesday, 14 June 2017 12:51

 

የሹምሽሩ ሰዓት እንዳበቃ ግርማዊ ጃንሆይ ወደ ወርቃማው አዳራሽ ይሄዳሉ። እዚህ አዳራሽ ውስጥ የገንዘብ ሣጥኑ መከፈቻ ሰዓት ይጀምራል። ይህም ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ያለው ጊዜ ነው። በዚህ ሰዓት ጃንሆይ በአባ ሃና ይታጀባሉ። እሳቸው ደግሞ ታማኝ ቦርሳ ያዢያቸውን ያስከትላሉ። አንድ አስተዋይ አይንና አድማጭ ጆሮ ያለው ሰው በቤተ መንግስቱ የገንዘብ ሽታ ሲሸት ምን ያህል ረፍተ ቢስ እንደሚሆን ማስተዋል ይችላል። ገንዘብ በአዳራሽ ተበትኖ አይገኝም። ግርማዊነታቸውም ገንዘብን ዝም ብሎ የመበተን ሃሳብ የላቸውም። ገንዘብ ለማግኘት የረቀቀ ምክንያትና ስሜትን ይጠይቃል።

ምንም እንኳ ውድ ወዳጄ፤ ሃያልነታቸው ሊገመት የማይቻል ቢሆንም የአባ ሃና ትንሽ ቦርሳ ማለቂያ የሌለው ገንዘብ ትይዛለች። የስነ ስርዓቱ ኃላፊ ጃንሆይ በገንዘብ እጥረት እንዳይሸማቀቁ ነገሮችን በጥንቃቄና በእቅድ መያዝ ይገባዋል። ለምሳሌ ጃንሆይ ለውጭ አገር ዜጋ ሰራተኞች እንዴት ይከፍሉ እንደነበርና ገነተ ልዑል ቤተመንግስት ተሰብስበው ክፍያቸውን ሲጠይቁ ያደረጉትን አስታውሳለሁ።

የቤተመንግስቱ ግቢ ኃላፊ መጥቶ ለግንበኞቹ ወደቤተመንግስቱ ጀርባ እንዲሄዱና እዚያ ጃንሆይ በገንዘብ እንደሚያንበሸብሿቸው ነገሯቸው። ምስኪኖቹ በደስታ እየቦረቁ ወደ ጀርባ ሄዱ። ይህ ጃንሆይ ክብራቸው ሳይነካ በፊት ለፊቱ በር ወጥተው ወደ አሮጌው ቤተመንስት ለመሄድ መንገዱን ክፍት አደረገላቸው።

                        (ሚስጥራዊው ንጉሥ - ከዮሐናን ካሳ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
291 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 749 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us