ፈረንጅ የሚያስመስል በሽታ

Wednesday, 21 June 2017 13:31

በአዲስ አበባው የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምር ዘንድ የተፈቀደለት አንድ የእንግሊዝ አገር ፈረንጅ በትምህርት ክፍል ገብቶ ሲያስተምር “ለምጽ ማለት ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፡፡ ከአራት ኪሎ አካባቢ አዳጊ ልጆች መካከል አንዱ ሲመልስ “ለምጽ የሰውነትን ቆዳ በመለወጥ ፈረንጅ የሚያስመስል በሽታ ነው” አለው፡፡ ፈረንጁ በብርቱ ተናዶ ከብስጭት ብዛት የተነሳ ቁጣው እየጦፈ “እናንተ ኢትዮጵያውያን የቅኝ ግዛትን አለንጋ ስላልቀመሳችሁ እንደዚህ እንደልባችሁ ስትናገሩ ትኖራላችሁ፡፡ እኔ አሁን ኬንያ ብሄድ እንደ ታላቅ ንጉሥ ሆኜ ነበር የምከበረው” ሲል አዳጊው ልጅ ነገሩን በማባባስ “ታዲያ እዚያው እለመዱበት አገር ለምን አይሄዱም?” አለው፡፡

ፈረንጁ ቢቸግረው “ይህ የስድብ ቃል ሲነገር የሳቃችሁ ተማሪዎች ሁሉ ተንበርከኩ” አለ፡፡ ተማሪዎቹ እየሳቁ ለዚያ ፈረንጅ በጉልበታቸው ሲንበረከኩለት በኩራት የተሞላ አልበገር ባይ ልባቸው ግን ሊንበረከክለት አልፈቀደም፡፡ እነሆ ገና በማደግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ልጆች (Teenagers) አእምሮ እንኳ ተቀርጾ የሚኖር ከደም የተወረሰ የኢትዮጵያዊነት የተፈጥሮ አርበኝነት ሥነ ባህርይና ወኔ ይህን የሚመስል በመሆኑ ለዘለዓለም ያኮራናል” ብንል ማጋነን አይሆንም፡፡ አዎ፡፡ ፈረንጁ እንዳለው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በኬንያ አንድ ጥቁር የሀገር ኗሪ ምግብ ቤት (ሆቴል) ገብቶ ምግብ ካዘዘ በኋላ ፈረንጅ ከገባ በቅድሚያ የሚስተናገድ ፈረንጁ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ደማቸው እየፈላ በናይሮቢ ቦክስ እስከመምዘዝ ደርሰዋል፡፡

    (“ልዩ የአርበኝነት ባሕር ሲደመር ወታደራዊ ክሂል”፤ በመጋቢ አእላፍ መክብብ አጥናው) 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
222 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 941 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us