መርከበኛውና ባህሩ

Wednesday, 21 June 2017 13:51

 

በድሮ ጊዜ አንድ መርከበኛ ነበር፡፡ ይህም መርከበኛ በመርከቡ ሩቅ አገር ሳይቀር እየተጓዘ በመንገድ ይኖር ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ግን ኃይለኛ ማዕበል ተነሳና መርከቡን እያላጋ ወስዶ እባህር ዳርቻ ላይ ወረወረው፡፡ መርከቡም እንደገና ተመልሶ ሊጠገን በማይችል ሁኔታ እንክትክቱ ወጣ፡፡ በመርከቡ ውስጥ የነበረው ሀብትም ምንም ሳይቀር ባህሩ ዋጠው፡፡ መርከበኛው ራሱ ህሊናውን ለብዙ ሰዓታት ስቶ ወደቀ፡፡ የት እንዳለና ምን እንደደረሰበት ሲያስታውስ ግን ተነስቶ ባህሩን መርገም ጀመረ፡፡

በዚህ ጊዜ ከባህሩ አንዳች ምስል በውሃ ሲሰራ ታየ፡፡ ምስሉም ወደሴት ምስልነት ተቀየረ፡፡ የባህሩ ምስልም “ስማ መርከበኛው እንደምታውቀው ሁሉ ውሃ ፀጥ ያለና ሰላማዊ ነው፡፡ ነገር ግን ነፋስ በሰላም ወደሚኖርበት እየመጣ ማዕበል እንዲፈጥር ያደርገዋል፡፡ ማዕበል ሲፈጠርም እንደምታየው ባህርን ያናውጠዋል፡፡ ስለዚህ መርገም ያለብህ ነፋስን እንጂ ባህርን አይደለም” አለው፡፡

በዚህም ምክንያት መርከበኛው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደድህነት የለወጠውን ማዕበል ረገመው፡፡ ማዕበልም እንደባህር ሁሉ ወደ ሰው ምስል ተቀየረና “ስማ ማዕበልን በከንቱ አትርገም፡፡ ማዕበል ማለት አየር ማለት ነው፡፡ አየርም የተፈጥሮ ግዴታው ስለሆነ ከሞቃት ወደ ቀዝቃዛ ይሄዳል፡፡ እናም የተፈጥሮ ግዴታውን ለመወጣት ሲሄድ ማዕበል ይፈጠራል፡፡ ስለዚህ ሙቀትና ቅዝቃዜን የምትፈጥረውን ጸሐይን እንጂ እኔን መርገም አይርብህም” አለችው፡፡

ሰውየው ፀሐይን መርገም ጀመረ፡፡

ፀሐይም “ስማ መርከበኛው እኔም የማሞቀውና የማቀዘቅዘው የተፈጥሮ ግዴታዬ ስለሆነ ነው፡፡ ብርሃን ስሰጥ እንደምትጠቀመውና ጨለማ ሲሆን እንደምታርፈው ሁሉ በሙቀትና ቅዝቃዜም ተጠቃሚ ነህ፡፡ ነፋስ ባይነፍስ መርከብህ በንፋስ ኃይል አይጓዝም፡፡ ውሃም ባይናወጥ ይሸት ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር ያለምክንያት አልተፈጠርምና ጊዜህን በመራገም አታባክን፡፡ ይልቅ ሕይወትህ በመትረፉ ፈጣሪህን አመስግን፡፡ ባለፈው ሳትቆጭም ተነስተህ በአዲስ መንፈስ ለመሥራት ጣር” አለችና መከረችው፡፡

መርከበኛውም ፀሐይ የተናገረችው እውነት መሆኑን አምኖ በአዲስ መንፈስ ጠንክሮ መሥራት ጀመረ፡፡ ከድሮው የበለጠም ሀብታም ሆኖ ኖረ፡፡

                        (“የኤዞፕ ተረቶች” - ተሾመ ብርሃኑ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
228 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 914 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us