ምርጥ አባባሎች

Wednesday, 28 June 2017 11:48

 

- ጨቋኞችን መታገል እግዚአብሔን መታዘዝ ነው። / ቤንጆሚን ፍራንክሊን/
- እያንዳንዱ ትውልድ በአባቶች ላይ ያምፃል፤ ከአያቶቹ ጋር ይወዳጃል። /ልዊስ ማምፎርድ/
- ሳሩ ለምለም ሲሆን ማንም ስለበጋ አያስብም። /ሩድያርድ ኪፕሊንግ/
- ፍቅር ማለት እውነት ማለት ነው። እውነት የጨበጠች ነፍስ ከማንም በላይ የፍቅር ባለፀጋ ነች። /ሚክሎ/
- በህይወት የሚያጋጥም እውነተኛ ድክመት አንድ ብቻ ሲሆን እሱም ልብ የሚያውቀውን እንደማያውቅ መምሰል ነው። /ፍሬዴሬክ ፉለር/
- ጠባይህ መጥፎና ዋጋ ቢስ ከሆነ የደስታ መንፈስና ኩራት ሊኖርህ አይችልም። /ዲሞስቴን/
- የሞኝ ሰው ልቡ አፉ ነው። የብልህ ሰው አፉ ግን ልቡ ነው። / ፍራንክሊን/
- እንደ ልጆች ስላለፈውና ወደፊት ስለሚመጣው የማይጨነቁ ጥቂቶችና ዛሬን የሚደሰቱ እድለኞች ናቸው። /ላብፋየር/
- ምርጥ የሰው ስሜት የሚባለው በቃላት ለመግለፅ ሲያቅትህ ነው። /ማቸሊሐመር/
- ማንም ሰው የተፈጠረው ለፍቅር ሲሆን በዚህ ረገድ ያለው ግንዛቤ ጊዜ የማይሽረውና ቀጣይም ነው። /ዶዝሬየሊ/
- አነስተኛ የፍቅር ስጦታም ቢሆን መልዕክት አለው በቅንነትም ለመቀበል ቀላል ሁኔታ አይደለም። ይህ ከሆነ መልካም ሀሳብ የታጀለበተና በፍቅር ቋጠሮ የተማከለ ነው። /ኤል ኦ ቡየር/
                                                         (“ንጥር” የዓለም ድንቃድንቅ አባባሎች፤ ከአሰፋ ሽፈራው)

ይምረጡ
(6 ሰዎች መርጠዋል)
1604 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us