ስለፍቅር ሲባል. . .

Wednesday, 28 June 2017 11:51

 

በሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በጥንታዊ አረብ የአንድ ጎሳ መሪ ልጅ ስሙ ቃይስ ይባል ነበር። ቃይስ ሌያላ የምትባለውን ወጣት ሴት አፍቅሮ እስከሚያብድ ድረስ መልከ መልካምና ጎበዝ ወጣት ተብሎ ይደነቅ ነበር። አንድ ቀን ቃይስ ሰክሮ ከትምህርት ቤት ወጥቶ በየመንገዱ የሌያላን ስም እየጠራ በመሄዱ መጅነኑ ወይም እብድ እየተባለ ይጠራ ጀመር። ጥቂት ቆይቶ በረሃው ውስጥ ገብቶ አሸዋ ላይ ራቁቱን ከእንስሳት ጋር መኖር ጀመረ። በረሃ ውስጥ እያለ ስለፍቅረኛው ግጥም እየገጠመ ዘፈን ይዘፍን ነበር። ሌያላም ሌሊት ከአባቷ መኖርያ ድንኳን ቀስ ብላ ወጥታ የፍቅር ደብዳቤ እየፃፈች በመንገደኛ ለቃይስ ትልክ ነበር። ሁለቱ ፍቅረኞች ከተለያየ ጎሳዎች በመወለዳቸው መጋባት የማይታሰብ ነበር። ሆኖም ውሎ አድሮ ግንኙነት እንዳላቸው እየታወቀ ሄደና ሁለቱም ጎሳዎች በነዚህ ፍቅረኛሞ የተነሳ ጦርነት ይከፍቱና ፍቀረኛሞቹም ሆነ ሌሎች ብዙ ሰዎች ይሞታሉ። ይሄ ታሪክ ብቻ ለቀሪው ትውልድ ይተላለፋል።


በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቻይና ውስጥ ትኖር የነበረችው የአስራ አምስት ዓመት ወጣት ሚሌን ለፍቅር ስትል በሞት አፋፍ ላይ ትኖር ነበረ። አባትዋ ባለስልጣን ከመሆኑም ሌላ የወደደችው ወጣት ከዝቅተኛ መደብ የተወለደ ነበር። ሚሌንና ቻንግ ፖ ከተለያየ መደብ ስለመጡ መፋቀርና መጋባት ቀርቶ አብሮ መታየት ፍፁም የማይታሰብ ነበር።


አንድ ቀን ጠዋት ቻንግ ፖ እንደ ላሊበላ በፍቅረኛው ቤተሰቦች በራፍ ላይ የሚከትለውን እያለ ይለፈልፍ ነበር መሬትና ሰማይ ከተፈጠሩ ጀምሮ አንቺ ለኔ እንደተሰራሽው እኔም ላንቺ ስለተሰራሁ አንቺን አሳልፌ ለሌላ አልሰጥም” ብሎ ጠልፎአት ይዟት ይሄዳል። ሆኖም ብዙ ሳይቆይ ከተደበቁበት ፈልገው ሲያገኟቸው እሱ ሲያመልጥ እሷ ግን በህይወቷ ተቀበረች። ድርጊቱ ግን በሚለየን ለሚቆጠሩ ቻይናውያን ፀፀትን አትርፏል።
(“ፍቅር ምንድነው?” ከወንድሙ ነጋሽ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
512 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 922 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us