አሳልፉኝ

Wednesday, 05 July 2017 12:30

 

ያ ለጋው እኔነቴ፣ የሕሊና ቀንበጥ ሲያቆጠቁጥ

የፊደልን ዘር ዘግኖ፣ በረድፍ በተራ ሲገጠግጥ

የመሆንን ሰምና ወርቅ፣ ስምና ግሱን ሲተረትር

ያልተገራውን አእምሮ፣ በዕውቀት አለንጋ ሲሰግር

ህልሙን ለመኖር ነበር፣ በ“እሆናለሁ” ሙሻዘር

 

አልሞም አላበቃ፣ ሌላ ሕልምን ጠነሰሰ

እንደ ‘ሚንዶሎዶል ፏፏቴ

በ“እሆናለሁ” ስውር ዓለም፣ ‘ባሳብ ፈረስ ገሰገሰ

ገስግሶም አላቆመ፣ ከቅጥሩ ደረሰ

ደርሶም ብቻ አላበቃ፣ እበራፉ ፈሰሰ

 

በደፉ ላይ ተሰትሮ

ከጥበብ ጥርብ ምሰሶ፣ እደጃፉ ተገትሮ

ረጅም ሕልም

ሩቅ ሃሳብ፣ ቸልታውን ‘ንደዘረጋ

አምናም፣ ካቻምናም፣ ለመኸር

ዳግም ራስን ፍለጋ

 

እንደ ሰዓታት ዘንግ፣ ማይጓደል ግብሩ

ሲሽከረከር አለ፣ የጥረቴ ጡዘት፣ የህልሜ ምህዋሩ   

(ምንጭ- “በዘመን ጥላ ሥር” ስብስብ ግጥሞች፤ በፍጹም አማረ)

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
200 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 914 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us